Skip to content
Facebook Twitter
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring & Investigation
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ኢሰመኮ የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅዱን በይፋ አስተዋወቀ

November 24, 2021February 20, 2022 EHRC Quote

ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኅዳር 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚካሄድና መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት ስብሰባ የኮሚሽኑን የአምስት ዓመት ስትራቴጂ እቅድ በይፋ አስተዋውቋል።  ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የስትራቴጂ እቅዱን አዘገጃጀት ሂደት አስመልክቶ  “የኮሚሽኑን ሰራተኞችና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና ምክክር፣ እንዲሁም ነባራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል” ብለዋል። የስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅቱ የመጨረሻ ውጤት በኮሚሽኑ አመራር እና በሁሉም ሰራተኞች ዘንድ በባለቤትነት እንዲያዝ ብሎም በስኬት የመተግበሩን ዕድል በሚጨምር መልኩ አሳታፊ እና ምክክርን መሰረት ባደረገ ሁኔታ የተከናወነ ነው፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

“ይህ የስትራቴጂ ዕቅድ ኮሚሽኑ በተሰጠው ስልጣን እና ኃላፊነት መሰረት የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንዲመራ፤ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት (2014-2018) ካሉት እና ወደፊት ሊከሰቱ ይችላሉ ከሚባሉ ብሔራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች አንጻር ስልታዊ/ስትራቴጂያዊ ትኩረት እንዲኖረው ለማስቻል ታልሞ” መዘጋጀቱን የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ አስረድተዋል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ

የስትራቴጂ እቅዱ ዋና ዋና ይዘቶች በኅዳር 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በተዘጋጀው ስብስባ ለተሳተፉ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማትና የኢሰመኮ አጋር ድርጅቶች ቀርበዋል። በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚሰራ በመሆኑ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ በአሶሳ፣ በባሕርዳር፣ በጋምቤላ፣ በሀዋሳ፣ በጅማ፣ በጅግጅጋ፣ በመቀሌ እና በሰመራ ከተሞች ስምንት ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች እንዳሉትና ስትራቴጂክ እቅዱን ለማስፈጸም የሚያስችለው አዲስ መዋቅር ተቀርጾ ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።

ስለሆነም የኮሚሽኑ ዓላማ ፈጻሚ የስራ ክፍሎች የሰብአዊ መብቶች ትምህርት፣ የሰብአዊ መብቶች ምርመራና ክትትል፣ የሴቶችና ሕጻናት መብቶች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች፣ የስደተኞች የተፈናቃዮችና ፍልሰተኞች መብቶች፣ የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች፣ እና የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የዋና ኮሚሽነሩን ጽ/ቤት ጨምሮ በሕግና ፖሊሲ፣ በሚዲያና ኮሚሙኒኬሽን፣ በእቅድና አጋርነት፣ በሰው ሃብት፣ በፋይናንስና አስተዳደር፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብር ድጋፍ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች እንዳሉት ተነግሯል።

የኮሚሽኑ ስትራቴጂክ እቅድ የኮሚሽኑን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች እና መርሆዎች መሰረት በማድረግ፣ የኮሚሽኑን ስትራቴጂካዊ ተቀዳሚ ተግባራት (Strategic Priorities) ለይቷል። የኢሰመኮ ራዕይ “ሰብአዊ መብቶች ባሕል የሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት” ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ገለልተኝነት፣ አካታችነት፣ አጋርነት እና ለተጎጂዎች/ለጉዳት ተጋላጭ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጎን መቆም  በሚሉ ዋና ዋና እሴቶች የሚመራ ይሆናል።

ስትራቴጂክ እቅዱ ያስቀመጣቸው አምስት ቁልፍ የውጤት መስኮች መሰረት ያደረገ ዝርዝር የአፈጻጸም መርኃ ግብሮች ተዘርዝረዋል። እነሱም፡

  • በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እንዲኖር ማስቻል፣
  • የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራን በማጐልበት ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ አይነተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ፣
  • የቅድሚያ ትኩረት በተሰጣቸው የዘርፍ ጉዳዮች ውጤታማ የሆነና የሁሉም የሰብአዊ መብቶች ዘርፎችን መስፋፋት፣ መከበርና እና ጥበቃ እንዲኖር ማስቻል፣ 
  • ኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነቱን የሚያሳካ ተቋማዊ አቅም እንዲኖረው የሰው ሃብት፣ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን አቅምና ስልቶች ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የተቋም አቅም ግንባታ ስራዎች ማከናወን ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኮሚሽኑ ተቋማዊ አሰራሩ አካታች (inclusive) መሆኑን ለማረጋገጥም  በሁሉም የኮሚሽኑ ተግባሮችና አገልግሎቶች  ውስጥ ሥርዓተ ፆታ፣ የአካል ጉዳተኝነት መብቶችንና የብዝሃነት መርሆች መካተቱን ማረጋገጥ፣ 
  • እንዲሁም አጋርነትን (Partnership) በተመለከተ ኮሚሽኑ ዓላማውን ለማስፈጸም ይረዳው ዘንድ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እና የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ጨምሮ ተባብሮ መስራት መሆናቸውን ተገልጿል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው መድረክ “ለሰብአዊ መብቶች መከበርና መስፋፋት ጠቃሚና አካታች የሆኑ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት፣ ከድሮው በበለጠ አብሮ ለመስራት መንገዶች የሚከፈቱበት መድረክ እንደሚሆን” ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል፡፡

Related posts

January 17, 2022February 12, 2023 Event Update
በታኅሣሥ እና በጥር ወራት 2014 ዓ.ም. ከተከናወኑ አበይት ተግባራት በጥቂቱ
December 7, 2021December 7, 2021 Press Release
EHRC thanks its stakeholders for their support in its success in obtaining “A” status reaccreditation
December 10, 2021February 15, 2023 EHRC Quote
ኢሰመድህ ከተ.መድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምስራቅ አፍሪካ ጽ/ቤት (UNOHCHR - EARO) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርኃ ግብር ለኢሰመኮ ምስጋና አቀረበ
June 18, 2021February 12, 2023 Press Release
በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብአዊ መብቶችን አክብረው መንቀሳቀስ አለበቸው

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.