የኢ... ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 18(1) 

  • ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው። 

የማሰቃየት እና ሌሎች ሰብአዊና ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 16 

  • እያንዳንዱ ስምምነቱን የተቀበለ ሀገር የማሰቃየት ትርጓሜን የማያሟሉ ሌሎች ጭካኔ የተሞላባቸው  ኢሰብአዊ፣ አዋራጅ ድርጊቶች በቁጥጥሩ ስር ባለ ማንኛውም ግዛት በመንግሥት ባለሥልጣናት ወይም በሌላ ሥልጣን በተሰጠው ግለሰብ ወይም በእርሱ አነሳሽነት ወይም አውቆ ባለመቃወም እንዳይፈጸሙ የመከላከል ግዴታ አለበት።