Skip to content
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Human Rights Monitoring and Investigation
        • Women’s and Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ረቂቅ የግብረገብ ትምህርት ከሪኩለም (መማሪያ) ውስጥ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ማስረጽ ስለማስቻል

June 10, 2022October 6, 2022 Event Update

የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እራሱ ሰብአዊ መብት እንደመሆኑ ሰብአዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ ትምህርት በሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት የማድረግ ጥረት የአትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገር አቀፍ ደረጃ ከገባው ግዴታ ጋር የሚያያዝ ነው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች የተረቀቀውን የግብረገብ ትምህርት መማሪያ (ከሪኩለም) ለሚገመግሙ ባለሙያዎች በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ግንቦት 29 እና 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ አዘጋጀ። 

ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአፋር፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፣ ከመንግሥትና ከግል ትምህርት ቤት እና ከኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ኅብረት ተወካዮች በስልጠናው ተሳትፈዋል። በተጨማሪም የግብረገብ ትምህርት መጻሕፍትን ያረቀቁ የባሕር ዳር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የስልጠናው አካል ነበሩ።

ስልጠናው በሰኔ ወር መጀመሪያ በሚካሄደው የውይይት መድረክ፣ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚማሩባቸው እና በትምህርት ሚኒስቴር በተቀጠሩ የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተረቀቁት የግብረገብ መጻሕፍት ላይ አስተያየት የሚሰጡ ተሳታፊዎች ከሰብአዊ መብቶች አንጻር አስተያየት ለመስጠትና ለመገምገም እንዲችሉ አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው። በተጨማሪም ኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ለሚያደርገው ጥረት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል የሚያግዝ ነው።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት የቆየው ስልጠና የተለያዩ ግን ተዛማጅ ሦስት አበይት ክፍሎች ተከፍሎ ለሰልጣኞች ቀርቧል። ስለ ሰብአዊ መብቶች ምንነት፣ ባሕሪያት እና እሴቶች በመጀመሪያው ክፍል የተዳሰሱ ሲሆን፣ ሁለተኛው ክፍል የግብረገብ እና የሰብአዊ መብቶች እሴቶች ምንነት፣ ግቦች፣ ተዛማጅነትና ተደጋጋፊነት ላይ ያተኮረ ነበር። አሳታፊ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ዘዴ እና ክህሎት ለግብረገብ ትምህርት አሰጣጥ ያለውን ጠቀሜታ ተገባራዊነት በመጨረሻው ክፍል ተዋውቀዋል ።

የስልጣናው ተሳታፊዎች የግብረገብ  ትምህርት መጻሕፍትን ለመገምገም የሚያስችል አዳዲስ ግንዛቤዎችን እና መረጃዎችን ለማግኘት እንደቻሉ የተናገሩ ሲሆን፤  የተማሪዎችን እውቀት፣ አመለካከት እና ችሎታ ለማሳደግ እና ወደፊትም ተማሪን ያማከለ ዘዴን ለመጠቀም ያላቸውን ተነሳሽነት ገልጸዋል። አክለውም የኢሰመኮ እና ትምህርት ሚኒስቴር በትብብር መስራታቸው አበረታች ጅማሮ መሆኑን ገልጸው ለወደፊቱ መጻሕፍት ከመረቀቃቸው ቀደም ብሎ ይህን መሰል ስልጠናዎች ቢዘጋጁ ውጤቱ የላቀ እንደሚሆን አመላክተዋል።

የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና  ማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጂብሪል

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና  ማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጂብሪል፣ “ሰብአዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ ትምህርት በሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት የማድረግ ጥረት የአትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገር አቀፍ ደረጃ ከተገባው ግዴታ ጋር የሚያያዝ ነው” ብለዋል። በሂደት በሀገራችን ውስጥ ሰብአዊ መብቶችን ባሕሉ ያደረገ ዜጋ ለመፍጠር  ከፍተኛ  አስተዋጽዖ እንደሚኖረው አክለው ገልጸዋል፡፡

Location Ethiopia

Related posts

August 26, 2021February 12, 2023 Press Release
ምስራቅ ወለጋ፡ የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሊጠናከር ይገባል
March 9, 2022March 9, 2022 Human Rights Concept
Gender Equality and Human Rights
April 28, 2022October 6, 2022 Event Update
ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምስለ ፍርድ ቤት ውድድር ክልላዊ ምዕራፍ በ12 ከተሞች በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙሪያ ላይ አተኩሮ ተካሄደ
April 29, 2022October 6, 2022 Press Release
የአፍሪካን ቅድመ-ክስ ወይም ቅድመ ፍርድ እስራት ቀን ለማሰብ ኢሰመኮ እና አጋር ድርጅቶች በመተባበር ከወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት ከፍተኛ ተወካዮች ጋር የተደረገ ውይይት

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on TwitterYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on Linkedin

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • EHRC Visuals
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
 

Loading Comments...
 

    Search
    Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.