ስለ እኛ


የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ስደተኞች ከሚያስተናግዱ አገሮች አንዷ ከመሆኗ በተጨማሪ፣ በርካታ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ያሉባት እና የፍልሰተኞች አመንጭ፥ መተላለፊያና መዳረሻም ሀገር ናት። ስለሆነም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ የስደተኞችንና ፍልሰተኞች መብቶች ማክበር እና ማስከበር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ከሚገባው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው።

በዚህ ረገድ ሊሰራባቸው የሚገቡ ስትራተጂያዊ ጉዳዮች የምርምር ስራና ውትወታ፤ እነዚህ ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች መብቶቻቸውን ማስከበር እንዲችሉ የማብቃት ስራ መስራት፤ የእነዚህን የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከቱ ዓለም አቀፍና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች እየተተገበሩ መሆናቸውን መከታተል፤ እንዲሁም የሰብአዊ መብቶቹን አተገባበር ለማሻሻል እና እነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚገባቸውን ጥበቃ በተመለከተ ከባለድርሻ አካለት ጋር ትብብር መፍጠርና በጋራ መስራትን ያጠቃልላል።