የሳምንቱ የሰብአዊ መብት ጽንሰ-ሀሳብ
ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 2፣ 2014 ዓ.ም.

የአፍሪካ የሰብአዊና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) ሀገራት ማንኛውንም አይነት አድሏዊ አሠራር የሕግ፣ ተቋማዊ እና ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎችን በመውሰድ እንዲያስወግዱ ያለባቸውን ግዴታ ደነግጋል፡፡  

የሴቶች እና የወንዶች/ሴት ልጆች እና ወንድ ልጆች እኩልነት በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት እና ሀገሪቱ ፈርማ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ውስጥ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ሆኖም በሃገሪቱ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶችና ልጃገረዶች የሲቪል፣ የባህል፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ መብቶቻቸውን ለመጠቀም እንዳይችሉ ስር የሰደደ አድሎአዊ ልዩነት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡

የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ለዘላቂ ልማት!