Skip to content
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Human Rights Monitoring and Investigation
        • Women’s and Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፡እየተበራከቱ የመጡ ከአስተዳደራዊ መዋቅር እና ከድንበር መካለል ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች መንስዔነት የሚያገረሹ ግጭቶች ዘላቂ ምላሽ ይሻል

July 7, 2022October 6, 2022 Press Release

በግጭቶች የተጎዱ ሰዎችና አካባቢዎችንም መልሶ ለመጠገን እና ለማቋቋም በቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ያስፈልጋል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሲነሱ የነበሩ ከአስተዳደራዊ መዋቅር እና ከድንበር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በቅርበት ክትትል ሲያደርግ እና ለጥያቄዎቹ ተገቢ እና ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጣቸው ከተለያዩ አካላት ጋር ሲመካከር ቆይቷል።

በ2011 ዓ.ም. የሰገን አካባቢ ሕዝቦች በመባል ይታወቅ የነበረው ዞን በአዲስ መልክ ተዋቅሮ የቀድሞው ኮንሶ ወረዳ የዞን አስተዳደር ሆኖ ሲደራጅ፤ የተቀሩት በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን ስር የነበሩ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች አስተዳዳራዊ አደረጃጀት በምን ሁኔታ መቀጠል እንዳለባቸው ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ሳይሰጥ ቆይቷል። ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ የጉማይዴ ልዩ ወረዳ መመስረትን በሚደግፉ እና በማይደግፉ ነዋሪዎች መካከል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ ግምቱ በውል ያልታወቀ የነዋሪዎች ንብረት ወድሟል፡፡

ኢሰመኮ በታኅሣሥ ወር 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የክትትል ሪፖርት በአካባቢው በየወቅቱ የሚያገረሹ ግጭቶች ነዋሪውን ለተደጋጋሚ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እያጋለጠ መሆኑን አመላክቶ፣ የችግሩ መሰረታዊ ምክንያት ወይም የስር መንስዔ ገና እልባት ያላገኘና ግጭቱ መልሶ ሊያገረሽ የሚችል በመሆኑ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግና በተለይም ለተደጋጋሚ መፈናቀል የተዳረጉ እና በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው ለሚገኙ ሰዎች አስፈላጊውን ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ጥሪ ያቀረበ መሆኑ የሚታወስ ነው። በወቅቱም የክልሉ መንግሥት የኮሚሽኑን ምክረ ሃሳቦች በበጎ እንደሚቀበለው እና በሪፖርቱ ለተመላከቱ ችግሮች በአፋጣኝ እልባት እንደሚሰጥ የሚገልጽ ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ መካካል ባለው የእርሻ መሬት የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት በተለያየ ጊዜ በተፈጠሩ ግጭቶች የሰው ሕይወት መጥፋት፣ መፈናቀልና የንብረት ዘረፋ/ውድመት እየተፈጸመ ነው፡፡ ለምሳሌ በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. በተፈጠረ ግጭት የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ 11 ቤቶች ወድመዋል፡፡ የደ/ብ/ብ/ሕ ክልል መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ በአካባቢው የእርቅ ሥነ ሥርዓት ያካሄደ ቢሆንም፣ ግጭቶቹን በዘላቂነት ያላስቆመ መሆኑን እና በአካባቢው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መንስዔ ሆኖ መቀጠሉን መረዳት ተችሏል። 

በዚሁ አካባቢ በሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በደራሼ ልዩ ወረዳ ሀይበና ቀበሌ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን ለመያዝ በሚል የፀጥታ ኃይሎች ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት በኃላ ወደ አካባቢው በመምጣት በወሰዱት እርምጃ 5 ሰዎች ተገድለዋል፣ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል፣ እንዲሁም በርካታ ሰዎች ታስረዋል። በአካባቢው በተደጋጋሚ በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶችና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች አባላትን ጨምሮ የአካባቢው ሲቪል ነዋሪዎች ተገድለዋል፣ ትምህርት እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል፡፡

በደራሼ ልዩ ወረዳ ጋቶ ቀበሌ በ2011፣ 2013 እና 2014 ዓ.ም. በተለያዩ ጊዜያት በሚነሱ የኩስሜ ብሔረሰብ የራስ አስተዳደርና የመዋቅር ጥያቄዎች ምክንያት፤ ጥያቄውን በሚደግፉና በሚቃወሙ የመንደር 1 እና 2 ነዋሪዎች መካከል በተደጋጋሚ በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ቁጥራቸው ያልታወቀ የመንደር 1 ነዋሪዎች ተፈናቅለው ኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፉጩጫ ቀበሌ እና አካባቢው ተጠልለዋል እንዲሁም ሰብሎቻቸውና ቤት ንብረታቸው በእሳት ወድሟል። በተመሳሳይ በደራሼ ልዩ ወረዳ ጊዶሌ ከተማ እና በአካባቢው ከጋርዱላ ዞን መዋቅር ጥያቄ ጋር በተገናኘ ከየካቲት ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በተከሰቱ ግጭቶች ቁጥራቸው ገና ያልተረጋገጠ ነዋሪዎች፤ የፀጥታ ኃይሎች እና የመንግሥት አስተዳደር አባላት ሕይወት ጠፍቷል፤ እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ 

በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ አካባቢ ከየካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከአሪ ዞን መዋቅር ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት በደቡብ አሪ ወረዳ ቶልታ ቀበሌ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ 146 ቤቶችና አንድ መስጊድ ተቃጥለዋል፣ ንብረት ተዘርፏል። በደቡብ አሪ ወረዳ ጋዘር ከተማ መፀር፤ ባላመር፤ ባርካ፤ ውባመር ቀበሌዎች እና በሰሜን አሪ ወረዳ ሻንጋማ ቀበሌ፣ እንዲሁም በጂንካ ከተማ ቡርካመር ቀበሌ በተከሰተ ግጭት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ በብዙ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ እስከ 1,537 የሚሆኑ ሰዎች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ንብረታቸው በግጭቱ ምክንያት ወድሟል ወይም ተዘርፏል። 

በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁዴፓ) በ2013 ዓ.ም. ሀገራዊ ምርጫ ያሸነፈ መሆኑ የተገለጸ ቢሆንም፣ በምርጫ ውጤቱ መሰረት መከናወን የነበረበት የስልጣን ርክክብ ባለመፈጸሙ ለአለመግባባትና ለግጭት ምክንያት ሆኗል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በወረዳው የአስተዳደር አካላት በተወሰዱ እርምጃዎች ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር እንደተፈጸመፈ፣ የቀበሌ መታወቂያ እና የሴፍቲኔት ተጠቃሚነትን በመከልከል ሥልጣንን አለአግባብ የመጠቀምና የነዋሪዎችን ማኅበራዊ አገልግሎት የማግኘት መብት መንፈግ እንደተፈጸመ ኮሚሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ባደረገው ክትትል ተረድቷል፡፡ 

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ የአስተዳደራዊ መዋቅር እና ከድንበር ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚደረጉ ጥረቶች ሕብረተሰቡን በበቂ ሁኔታ ያላሳተፉ አልያም የዘገዩ መሆናቸውን፣ ይህ ደግሞ በሕብረተሰቡ ዘንድ የመገለል እና የመረሳት ስሜት እንዳሳደረ በተለያዩ ጊዜያት ለኮሚሽኑ ከቀረቡ አቤቱታዎች እና ኮሚሽኑ ካነጋገራቸው ነዋሪዎች መረዳት የተቻለ ሲሆን፤ ቅሬታዎቹ ለግጭቶች መነሳት ወይም መስፋፋት መንስዔ መሆናቸውን ጭምር አክለው ያስረዳሉ።

እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ የአስተዳደር አካላት በሕዝቡ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በአግባቡ በማስተናገድ ምላሽ አይሰጡም፣ የአስተዳደር አካላቱ “ጥያቄዎቹን የማድበስበስ፣ የማፈን፣ አሳንሶ የመመልከት እንዲሁም ጥያቄ አቅራቢዎችን የማሳደድ ሥራ” ይሰራሉ የሚሉ ቅሬታዎችን ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በተለያየ መልኩ ክትትል ባደረገባቸው አካባቢዎች የታጠቁ ግለሰቦች መንግሥትን ይደግፋሉ የተባሉ ግለሰቦችን፣ የፀጥታ ኃይሎችን እንዲሁም የመንግሥት አስተዳደር አባላትን መግደላቸውን፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ማድረጋቸውንም ተረድቷል፡፡

ስለሆነም በአንድ በኩል መፍትሔ ሳያገኙ በቆዩ የአስተዳደራዊ እና የድንበር ጥያቄዎች፣ በሌላ በኩል በአንዳንድ የአካባቢው አስተዳደር አካላት በሚወሰዱ የኃይል እርምጃዎች፣ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች በበቂ ሁኔታ አሳታፊ የሆነ አሠራር አለመኖር ለበርካታ ውስብስብ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት ሆኗል፤ ሲቪል ሰዎች እና የፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል፣ መንደሮች፣ ንብረት እና ሰብል በእሳት ወድመዋል። 

በመሆኑም መንግሥት የችግሩን ግዝፈት፣ ውስብስብነት እና እያስከተለ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመገንዘብ ነዋሪዎችን በበቂ ሁኔታ ያሳተፈ ዘላቂ መፍትሔ የማፈላለግ ተግባር በአፋጣኝ እንዲጀመር፣ እንዲሁም ግጭት በተከሰተባቸው የተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ተጠልለው ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በአፋጣኝ እርዳታና ድጋፍ እንዲቀርብና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ኮሚሽኑ በድጋሚ ያሳስባል። ጥያቄ አቅራቢዎች ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲያቀርቡና በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች፣ የአስተዳደር አካላት እና የፀጥታ ኃይል አባላት ተገቢ የወንጀል ምርመራ ተደርጎባቸው ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ሊደረግ ይገባል።

Location SNNP

Related posts

August 25, 2021August 26, 2023 EHRC Quote
ኢሰመኮ በአማራ ክልል የባለሞያ ቡድን ሊያሰማራ ነው
April 30, 2022October 6, 2022 Public Statement
Call to Prioritize the Establishment of a Minimum Wage System
September 24, 2021September 26, 2021 EHRC Quote
ኦሮሚያ ክልል: ግድያ እና መፈናቀል በምስራቅ ወለጋ
October 18, 2021February 12, 2023 EHRC on the News
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቆይታ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ጋር

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on TwitterYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on Linkedin

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.