Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በቂ ምግብ የማግኘት መብት

June 7, 2024June 11, 2024 Explainer

በቂ ምግብ የማግኘት መብት ምንድን ነው? በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዋና ዋና ይዘቶች (Components) ምንድን ናቸው? በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ስለ ምግብ መብት ምን ደንግጓል? ከበቂ ምግብ የማግኘት መብት የሚመነጩ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

በቂ ምግብ የማግኘት መብት ምንድን ነው?

በቂ ምግብ የማግኘት መብት ሰፊና በርካታ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች የሚዳስስ መብት ነው። የምግብ መብት የሚረጋገጠው በቂ ምግብ ለእያንዳንዱ ሰው ተደራሽ ሲሆን ወይም በግዢ ማግኘት  ሲቻል ነው። በመሆኑም በቂ ምግብ የማግኘት መብት አነስተኛውን የካሎሪ፣ የፕሮቲን መጠን እና ሌሎች ንጥረነገሮችን ማግኘት ላይ ብቻ ሳይወሰን በሰፊው መተርጎም እንዳለበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የኢኮኖሚ፤ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ኮሚቴ በአጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 12 እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት በመረጃ ሰነድ (fact sheet) ቁጥር 34 ያሳስባሉ። በቂ ምግብ የማግኘት መብት በራሱ መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ሲሆን ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች መከበርም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል። ሰብአዊ መብቶች እርስ በእርስ የሚደጋገፉ፣ የተዛመዱና የማይነጣጠሉ ከመሆናቸውም በላይ በቂ ምግብ የማግኘት መብት አለመከበር ሌሎች የሰብአዊ መብቶች እንዲጣሱ በር የሚከፍት ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ኮሚቴ በአጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 12 ላይ በሰጠው ማብራሪያ፣ በቂ ምግብ የማግኘት መብት ከሰው ልጅ የሰብአዊ ክብር ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንደሆነ እና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች ለተደነገጉ ሌሎች ሰብአዊ መብቶች መከበር ቁልፍ ሚና እንዳለው ያስቀምጣል።

በተጨማሪም በቂ ምግብ የማግኘት መብት ከማኀበራዊ ፍትሕ ተነጥሎ ሊታይ የማይችል፣ በሀገራትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድህነትን ለማስወገድ እና ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ለሁሉም ሰዎች እንዲከበሩ የሚያስችሉ ትክክለኛ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ፖሊሲዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግን የሚጠይቅ እንደሆነ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 12 ያስገነዝባል። በዚህም ምክንያት በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች እንዲሁም የብዙ ሀገራት ሕገ መንግሥቶች እና ሌሎች ሕግጋት ለምግብ መብት ዕውቅናና ጥበቃ ሰጥተውታል።

በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዋና ዋና ይዘቶች (Components) ምንድን ናቸው?

በአጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 12 እና በመረጃ ሰነድ ቁጥር 34 ላይ በተሰጠው ማብራሪያ መሠረት የምግብ መብት የሚከተሉት እርስ በእርስ ተያያዥነት ያላቸው ይዘቶች (Components) አሉት። 

1. የምግብ መኖር (Availability)

የምግብ መኖር ማለት እራስን ለመመገብ የሚያስችል ምግብ ምርታማ ከሆነ መሬት ወይም ከሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች እንዲሁም በገበያ ላይ ማግኘት የሚመላክት ነው።

2. ተደራሽነት (Accessibility)

ተደራሽነት ምግብ ዘላቂ በሆነ መልኩ ለግለሰቦች በኢኮኖሚ እና በአካል ተደራሽ ሲሆን ነው። ኢኮኖሚያዊ ተደራሽነት ምግብ ለማግኘት የሚወጡ ወጪዎች ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶችን ሥጋት ላይ የሚጥሉ እና አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖራቸው እንደማይገባ የሚያመላክት ነው። በተጨማሪም ተጋላጭ የኀብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም መሬት የሌላቸውን ሰዎች እና ሌሎች በድህነት ውስጥ ያሉ የኀብረተሰብ ክፍሎችን በተለየ መርኃግብር ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።

በሌላ በኩል አካላዊ ተደራሽነት ማለት በቂ ምግብ በአካላዊ ተጋላጭነት ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ማለትም ለሕፃናት፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአእምሮ ሕሙማን እና በከፍተኛ ሁኔታ የታመሙ ሰዎችን ጨምሮ ለሁሉም ሰው ተደራሽ መሆን እንዳለበት የሚያስረዳ ነው። እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች፣ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች እና ሌሎች በልዩ ሁኔታ የተጎዱ ሰዎች ልዩ ትኩረት ሲያስፈልጋቸው ከምግብ ተደራሽነት አንጻር ቅድሚያ የሚያገኙበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

3. በቂነት እና ዘላቂነት (Adequacy and Sustanability)

በቂነት እና ዘላቂነት ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው በቂ ምግብ የማግኘት መብት ይዘቶች(Components) ናቸው። በቂ ምግብ ማለት ለሰው ልጅ አካላዊ እና አእምሮአዊ እድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ምግብ በመጠንም ሆነ በጥራት የሰዎችን የአመጋገብ ፍላጎት ሊያረካ በሚችል መልኩ፣ ከባእድ ንጥረነገሮች በጸዳ ሁኔታ እና በተመጋቢዎች ባህል ተቀባይነት ባለው መንገድ ማግኘት ሲቻል ነው። በዚህ ውስጥ የግለሰቦችን ዕድሜ፣ የኑሮ ሁኔታ፣ ጤና፣ ሥራ፣ ጾታ፣ ወዘተ. ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል። ዘላቂነት ማለት ደግሞ ምግብ አሁን ላለውም ሆነ ለመጪው ትውልድ ተደራሽ በሆነ መልኩ መገኘት እንዳለበት የሚያመለክት ነው።

4. ተቀባይነት

ምግብ ተቀባይነት አለው የሚባለው የሸማች እና የባለመብቱን ባህላዊ ዕሴቶች ያገናዘበ ሲሆን ነው። በዚህም መሠረት ምግቡ በባለመብቱ ባህላዊ ዕሴቶች መመገብ የሚቻል መሆን አለበት።

በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው?

በቂ ምግብ የማግኘት መብትን ዕውቅና የሰጠው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ሰነድ ሁሉን አቀፍ/ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ሲሆን፣ ይህ ሰነድ ማንኛውም ሰው ለእራሱና ለቤተሰቡ ጤንነትና ደኅንነት በቂ በሚሆን የኑሮ ደረጃ የመኖር መብት እንዳለው ይደነግጋል። ይህም በቂ ምግብ የማግኘት መብትን ያካትታል።

ይህንን መብት የኢኮኖሚ፤ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን ከሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በተለየ ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ደንግጎት እናገኛለን። በዚህ ዓለም አቀፍ ሕግ አባል ሀገራት ማንኛውም ሰው በቂ ምግብ፣ ልብስ እና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ለራሱ እና ለቤተሰቡ በቂ በሆነ የኑሮ ደረጃ ለመኖር እና የኑሮውን ሁኔታ ለማሻሻል መብት ያለው መሆኑን ዕውቅና እንዲሰጡ ይደነግጋል። እንዲሁም አባል ሀገራት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የዓለም አቀፍ ትብብርን አስፈላጊነት ተገንዝበው የዚህን መብት ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስዱ ያስቀምጣል። በተጨማሪም ይህ ቃልኪዳን አባል ሀገራት ማንኛውም ሰው ሳይራብ ለመኖር ያለውን መሠረታዊ መብት በመገንዘብ በተናጠልም ሆነ በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት፡  

  • ቴክኒካዊና ሳይንሳዊ ዕውቀትን በመጠቀም የምግብ አመራረት፣ ክምችትና ስርጭት ዘዴን ለማሻሻል፣
  • የአልሚ ምግብ መሠረታዊ ዕውቀቶችን ለማሰራጨት፣
  • እጅግ የተመጣጠነ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አጠቃቀም እንዲኖር የግብርና ሥርዓቱን ለማሻሻል፣
  • ምግብ አስመጪና ላኪ ሀገሮች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ግምት ውስጥ በማስገባት በፍላጎታቸው መሠረት የተመጣጠነ የዓለም የምግብ አቅርቦት ስርጭት እንዲኖር ለማረጋገጥ ዝርዝር መርኃ ግብርን ጨምሮ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳሉ በማለት ይደነግጋል።

ከዚህ እንደምንረዳው ምንም እንኳ በቂ ምግብ የማግኘት መብትን የማሟላት ግዴታ የሚረጋገጠው በሂደት ቢሆንም ረሀብን ለመቀነስ እና ብሎም ለማስወገድ ሀገራት አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ዝቅተኛና መሠረታዊ ግዴታ እንዳለባቸው ነው።

ከላይ ከተጠቀሱት የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች በተጨማሪ በቂ ምግብ የማግኘት መብት በሌሎች የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችም ጭምር ዕውቅና ተሰጥቶታል። ለአብነት ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት እና ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት መጥቀስ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ የምግብ መብት በአፍሪካ ኅብረት የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችም ውስጥ ዕውቅና ያገኘ መብት ነው። ለምሳሌ የአፍሪካ ሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር በግልጽ በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዕውቅና ባይሰጥም ስምምነቱን የመተርጎም ሥልጣን ያለው የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን የምግብ መብት ከሌሎች መብቶች ሊመነጭ የሚችል በቻርተሩ ዕውቅና ያለው መብት መሆኑን ትርጓሜ ሰጥቶበታል።

የኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ስለ ምግብ መብት ምን ደንግጓል?

በቂ ምግብ የማግኘት መብት በኢትዮጵያ ሕጎች ውስጥ ዕውቅና የተሰጠው ሰብአዊ መብት ነው። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ከላይ እንዳየናቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በማያሻማ መልኩ በግልጽ ዕውቅና ባይሰጥም የሕገ መንግሥቱ የተለያዩ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ የምግብ መብት ዕውቅና እንደተሰጠው ያስረዳሉ። በተለይም የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 41 ስለኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ መብቶች ይደነግጋል። በዚህም መንግሥት የጤና፣ የትምህርት እና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል በማለት ደንግጓል። በተጨማሪም ሕገ መንግሥቱ የሀገሪቱ ዐቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የምግብ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል በማለት አስቀምጧል። በተጨማሪም ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 9 (4) ሥር ከላይ የተዘረዘሩት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች የሀገሪቱ የሕግ አካል እንደሆኑ ደንግጓል።

በሕገ መንግሥቱና በሌሎች ሕግጋት የተደነገገው የምግብ መብት በኢትዮጵያ ምግብን አስመልክቶ በወጡ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጅዎች አማካኝነት ለመተግበር ጥረት ተደርጓል። ከእነዚህም የምግብና ሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ፣ የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲ፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ እና የሰቆጣ ቃልኪዳን በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ከበቂ ምግብ የማግኘት መብት የሚመነጩ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

በቂ ምግብ የማግኘት መብት እንደ ማንኛውም ሰብአዊ መብቶች በመንግሥታት ላይ የሚከተሉትን ዋና ዋና ግዴታዎች ይጥላል።

የማክበር ግዴታ

የማክበር ግዴታ መንግሥት የሰዎችን በቂ ምግብ የማግኘት መብትን የሚያጣብብ ማንኛውንም እርምጃ ከመውሰድ እንዲታቀብና በሰዎች በቂ ምግብ የማግኘት መብት አላግባብ ጣልቃ እንዳይገባ የሚከለክል ግዴታ ነው።

የመጠበቅ ግዴታ

መንግሥት በቂ ምግብ የማግኘት መብትን የመጠበቅ ግዴታ አለበት ሲባል የሰዎች በቂ ምግብ የማግኘት መብት በሌሎች ሰዎች ወይም በድርጅቶች እንዳይጣስ ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ መውሰድ እንዳለበት የሚያሳስብ ነው።

የማሟላት ግዴታ

የመንግሥት የማሟላት ግዴታ መንግሥት ሰዎች የምግብ መብታቸውን መጠቀም እንዲችሉ አዎንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት የሚያስገነዝብ ግዴታ ነው። ይህም ማለት መንግሥት የተለያዩ የምግብ መብትን ለማስፋፋት የሚረዱ አስቻይ ሕጎችን እና ፖሊሲዎችን መቅረጽ ይጠበቅበታል። በተጨማሪም ሰዎች ከዐቅምቸው በላይ በሆነ ምክንያት ምግብ ማግኘት  ካልቻሉ መንግሥት በቀጥታ ምግብ የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል ማለት ነው። በአጠቃላይ የምግብ መብትን የማሟላት ግዴታ በሂደት ሊረጋገጥ የሚችል ቢሆንም መንግሥት ወዲያውኑ እንዲተገብራቸው የሚጠበቁ ግዴታዎች አሉ። ለምሳሌ መንግሥት ዜጎቹ እንዳይራቡ የማድረግ ግዴታ አለበት።

መንግሥት ከላይ የተጠቀሱትን ግዴታዎቹን በተለይም ዜጎቹን ከርሀብ ነጻ የማድረግ ዝቅተኛ ግዴታውን መወጣት ካልቻለ የምግብ መብት እንደተጣሰ ይቆጠራል። በተጨማሪም በሰዎች መካከል አድልዎ ማድረግ የምግብ መብትን የሚጥስ ድርጊት ነው።

Related posts

January 3, 2024January 3, 2024 Event Update
ምግብ በማግኘት መብት እና ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ አቀራረብ ላይ የተሰጠ ስልጠና
May 7, 2024May 7, 2024 Event Update
አዲስ አበባ፦ ምግብ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ የምገባ መርኃ ግብሮች ሚና እና ሰብአዊ መብቶች ተኮር አቀራረብ
February 16, 2022August 28, 2023 Human Rights Concept
ውሃ የማግኘት ሰብአዊ መብት
October 18, 2023October 23, 2023 Event Update
በምግብ ሥርዓት፣ ምግብ የማግኘት መብት እና ሰብአዊ መብትን መሠረት ያደረገ አቀራረብ ዙሪያ የተካሄዱ ስልጠናዎች

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.