The ethnic based attacks and counter-attacks in Amhara and Oromia, particularly in North Shoa and Oromia Special Zone, of recent weeks have claimed numerous lives and should be condemned.
These tragic incidents emanate from deep-rooted sociopolitical and institutional problems that require long-term sustainable solutions – measures that can break the cycle of gruesome violence that is taking place with impunity. The government should deliver on its responsibility to protect people.
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በተለይም በሰሜን ሸዋ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠሩና ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እና የአጸፋ ጥቃቶች የብዙ ሰዎች ሕይወት ያጠፋ ሲሆን አጥብቆ የሚወገዝ ነው።
እነዚህ አሳዛኝ ክስተቶች ጥልቅ መሰረት ካላቸው ማህበረሰባዊ፣ ፖለቲካዊ እና ተቋማዊ ምክንያቶች የሚመነጩ ሲሆኑ ያለተጠያቂነት እየተፈጸሙ ያሉትን ዘግናኝ ጥቃቶች በዘላቂነት ለማስቆም የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድን ግድ ይላሉ። መንግስትም የሰዎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል።