Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፣ ተጠያቂነትን ማስፈን እና ተጎጂዎችን መካስ ያስፈልጋል

August 4, 2025August 4, 2025 Press Release, Report

ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚያሳትፍ እና አካታች የሀገራዊ ምክክር፤ በሰብአዊ መብቶች መርሖች ላይ የተመሠረተ እና ተጎጂዎችን ማእከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራን ማረጋገጥ ይገባል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Download Download Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ባለ 152 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት በሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። ለ4ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ሪፖርት በበጀት ዓመቱ በየዘርፉ ባሉ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የተስተዋሉ ቁልፍ እመርታዎችን፣ አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ምክረ ሐሳቦችን እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያካተተ ነው።

ይህ ዓመታዊ ሪፖርት ኢሰመኮ በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች በተቋቋሙ የሥራ ክፍሎቹ በሰበሰባቸው ማስረጃዎች፣ ባከናወናቸው የክትትል እና ምርመራ ላይ መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው። በዚህም መሠረት ሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕን ጨምሮ የሲቪል እና የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ፣ የሴቶች እና የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች እና ፍልሰተኞች መብቶች፣ በኢሰመኮ የተስተናገዱ በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎችን ከመወጣት አኳያ ያለችበት ሁኔታን የሚያሳዩ ጉዳዮች በዝርዝር ተካተዋል።

በዚህ ሪፖርት ዘመን በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ አዎንታዊ አንድምታ ያላቸው ቁልፍ እርምጃዎች የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የተመላከቱትን ዋና ዋና ተቋማት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆች መቅረጽ፣ የዓለም አቀፍ ወንጀሎች ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም ተጎጂዎችንና ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ረቂቅ ስትራቴጂ ማዘጋጀት፤ የሀገራዊ ምክክር ሂደት እና አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይገኙበታል።

እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ለኢሰመኮ የውትወታ ሥራዎች አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ እርምጃዎች የተከናወኑ ሲሆን ለአብነት በአማራ ክልል ለዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ የሚሰጥ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶች የማጠናከሪያ አዋጅ መጽደቁ፤ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በ4 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ኢሰመኮ ከባለሥልጣኑ እንዲሁም እገዳ ከተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱ፤ በኦሮሚያ ክልል መንግሥትና “ጃል ሰኚ ነጋሳ” በተባለ ግለሰብ በሚመሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) አባላት መካከል ስምምነት መደረጉ እና ይህንን ተከትሎ በክልሉ የተወሰኑ ዞኖች ያለው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱ፤ “ወቅታዊ ጉዳይ” በሚል በተራዘመ እስር ላይ የነበሩ ሰዎች ከእስር መለቀቅ መጀመራቸው እና አዳዲስ ሕገ ወጥ እስራቶችም መቀነሳቸው መልካም እምርታ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክተዋል።

ሪፖርቱ በ2017 በጀት ዓመት የተስተዋሉ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችንም በዝርዝር አካቷል። በዚህ የሪፖርት ዘመን በአጠቃላይ በሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ የቀጠለው የትጥቅ ግጭቶች እንዲሁም የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ ነው። በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የትጥቅ ግጭት በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ የነጻነት እና ሌሎች የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ጥሰቶች ማስከተሉን ሪፖርቱ አመላክቷል። በተራዘመ የግጭት ዐውድ ውስጥ በተፋላሚ ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ በሰዎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን፤ የእገታ ተግባራት ተስፋፍተው መቀጠላቸውን፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍም ጥሰቶች መመዝገባቸውን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ገልጿል። እንዲሁም አልፎ አልፎ በሚያገረሹ ግጭቶችና የጸጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በሰዎች ላይ የሞት፣ አካል ጉዳት እና እገታ መድረሱን፤ በተወሰኑ አካባቢዎችም የእንቅስቃሴ ገደቦች መደረጋቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ከጸጥታ ችግሮች በተጨማሪ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ለሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል፣ የንብረት ውድመት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት መሆናቸው፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው እና በርካታ ትምህርት ቤቶችም አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው በሪፖርቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ሆነው ተካተዋል። በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በስፋት የተከሰቱ የወባ፣ ኮሌራ እና ኩፍኝ በሽታዎች በጤና መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸው፣ ከጤና ባለሙያዎች የደመወዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ የሙያ ዕድገት ዕድሎች እንዲሁም ምቹ የሥራ ቦታ እና ነጻነት ጥያቄዎች በወቅቱ አለመመለስ ጋር ተያይዞ በበጀት ዓመቱ የተከሰተው የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ በጤና መብት ዘርፍ ላይ ጉዳት ማስከተሉ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ሪፖርቱ የነጻነት መብትን በተመለከተ ካካተታቸው አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል በግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች በ“ኮማንድ ፖስት” እና በ“ወቅታዊ ጉዳዮች” በሚል የሚፈጸሙ እስሮች እና ተያያዥ የነጻነት መብት ጥሰቶች መቀጠላቸው፣ የአስገድዶ መሰወር ድርጊትን ወይም ያሉበት ሳይታወቅ ሰዎችን አስሮ የማቆየት ጥሰቶችን ሊያቋቁሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ጨምሮ የሕገ-ወጥ እስር ተግባራት አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎችም መፈጸማቸው ይገኙበታል። እንዲሁም በአብዛኛው የግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ/በቆዩ አካባቢዎች በታጣቂ ቡድኖች ወይም ሰዎች የሚፈጸሙ እገታዎች መከሰታቸውንና ይህም በነጻነት፣ የአካል ደኅንነት እና ሌሎች መሠረታዊ መብቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ሪፖርቱ አካቷል።

ኢሰመኮ በጥበቃ ሥር ያሉ(የታሰሩ) ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ በ66 ማረሚያ ቤቶች እና 473 ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም 9 መደበኛ ያልሆኑ ማቆያ ስፍራዎች ክትትል ያከናወነ ሲሆን በክትትሉ የለያቸው መልካም እመርታዎች እና አሳሳቢ ጉዳዮች በሪፖርቱ በዝርዝር ተመላክቷል። ሪፖርቱ ለኢሰመኮ የቀረቡ አቤቱታዎችን በተመለከተ በዝርዝር ያካተተ ሲሆን ኢሰመኮ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1524 ሰዎች በቡድንና በተናጠል ያቀረቧቸውን 1258 አቤቱታዎች ተቀብሎ ያስተናገደ መሆኑ ተገልጿል።

በ2017 በጀት ዓመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የጸደቀው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ማሻሻያ አዋጅ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ በሚዲያና የሲቪክ ምኅዳር ላይ እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትና የመደራጀት መብት ላይ ያላቸውን አንድምታ በዝርዝር ተመላክቷል።

ሪፖርቱ የሴቶችና ሕፃናት መብቶችን በተመለከተ ካካተታቸው አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል በአፋር እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚፈጸመው የሴት ልጅ ግርዛት ምክንያት የሴቶችና የሴት ሕፃናት በሕይወት የመኖር፣ የጤና፣ የአካል እና የአእምሮ ደኅንነት መብት እንዲሁም ከማንኛውም ኢሰብአዊ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ እና የሥቃይ እና የጭካኔ ተግባር የመጠበቅ መብቶቻቸውን ጨምሮ በርካታ መብቶቻቸው መጣሳቸውን፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ፋብሪካዎች የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዝርዝር የያዘ ነው።

በአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ዘርፍ በሪፖርቱ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል በልዩ አዳሪ እና አካቶ ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአካል ጉዳተኞች የከባቢያዊ፣ ተቋማዊና የመረጃ ተደራሽነት ችግር መኖር፤ በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መቀጠላቸው እና ይህንኑ ለማስቆምም የሚደረጉ ጥረቶች አነስተኛ መሆናቸው ተጠቃሽ ሲሆኑ በበጀት ዓመቱ የተስተዋሉ አበረታች እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸው።

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች እና ፍልሰተኞች መብቶችን በተመለከተ ሪፖርቱ ዝርዝር ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች በመጠለያ ጣቢያዎችና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው የሚገኙ ተፈናቃዮች እንዲሁም ተመላሾች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ፣ ተደራሽ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተፈናቃዮች ያማከለ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲሁም ትምህርትና ጤናን ጨምሮ የተሟላ ማኅበራዊ አገልግሎት የማይቀርብላቸው መሆኑ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ ለዳግም መፈናቀል የተዳረጉ ሰዎች መኖራቸው በበጀት ዓመቱ አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ ጉዳዮች መካከል ናቸው።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ መሻሻሎች የተመዘገቡባቸውን ዘርፎች በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ በሪፖርቱ በተሸፈነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በርካታ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ለመከሰታቸው እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋና ምክንያት የሆነውን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የትጥቅ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረሶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት ብቸኛው አማራጭ በመሆኑ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም በመጪው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚኖረውን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ መከበር እና መስፋፋት የተሻለ ለማድረግ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገና ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ትግበራን እና ሀገራዊ ምክክርን ማጠናከር፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በፈጸሙ አካላት ላይ ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ተጎጂዎች የሚካሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት (ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም.)
አንኳር ጉዳዮች:- የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት (ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም.)

Related posts

October 30, 2024October 30, 2024 Press Release
የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት
November 6, 2024January 23, 2025 Press Release
የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት
October 25, 2024October 28, 2024 Press Release
የሴቶች እና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት
September 6, 2023September 6, 2023 Press Release
የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶችን በተመለከተ አስቻይ የሕግ እና ተቋማዊ ማእቀፎች ሊቀረጹ ይገባል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.