በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ቡድን ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እና ከሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች አመራሮች እና ከድሬድዋ ከተማ አስተዳደር የከተማ ፍርድ ቤት ጋር በሰብአዊ መብቶች ማስፋፋትና ማከበር እንዲሁም የኢሰመኮ ተደራሸነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት አከናውኗል።

ቡድኑ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ እንዲሁም የሴቶች እና ህፃናት መብቶች ኮሚሽነር አሸነፈች አበበን ያካተተ ነው።

ውይይቱ የሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት ረገድ የፍርድ ቤቶች ሚና ማሳደግ በሚቻልበት እንዲሁም ኢሰመኮ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት ላይ ትኩረት መደረጉ ተገልጿል።

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሀዲን ተወፊቅ እንዲሁም የድሬድዋ ከተማ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ነጅብ ኢድሪስ በበኩላቸው፣ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በሀረሪ ክልላዊ መንግስት በሚገኙ የህፃናት ማሳደጊያዎች ላይ በኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በተደረገ ክትትል በጥቂት የህፃናት ማሳደጊያዎች ከህፃናት አያያዝና ሰብአዊ መብት አጠባበቅ አንፃር በተገኙ ግኝቶች አፋጣኝ እርምጃዎች መውሰድ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ከክልሉ የሴቶች የህፃናትና የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አመራሮች ጋር ዉይይት ተካሂዷል።