Areas of Work


የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕል መብቶች

በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕል መብቶች ረገድ ዋነና ተጎጂዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ እና የተገለሉ ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን፤ የተሻለ የኑሮ ደረጃን፣ የመኖሪያ ቤት እና የትምህርት መብቶችን ጨምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ቅድሚያ መስጠት ላይ ትኩረት ያደረገ ሰፊ የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚ መብቶችን የማስፋፋት፣ የማክበር እና የመተበቅ ተግባራትን ለማስፈጸም እንሠራለን።

በተጨማሪም የመብቶች እኩልነት፣ ሰብአዊ ክብር እና መድልዎ የሌለበት ሁኔታን በማረጋገጥ፤ በራስ ባሕል ተሳትፎ የማድረግ እና በራስ ቋንቋ ትምህርት የማግኘት መብቶችን ጨምሮ ከባሕል መብቶች ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ተጠቃሚነትን በማጎልበት የባሕል መብቶች ጥበቃ እንዲረጋገጥ እንተጋለን።

የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ድንጋጌዎች ግልጽነት፣ በፍርድ ቤት የመዳኘት፣ የማስፈጸም ዐቅም እና የመብቶቹ ተጠቃሚነት ላይ በምርምር እና በውትወታ የታገዘ ሥራን እንሠራለ፤ መብቶች ከሚጠይቋቸው የድንጋጌ መስፈርቶች ጋር ያለውን የተፈጻሚነት ደረጃ እንከታተላለን፤ እንዲሁም ሰብአዊ መብቶች የሚደጋገፉ እና የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሠራለን።