የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች
ከጠቅላላው የሕዝብ ቁጥር 17.6 በመቶ የሚሆነው ከተለያዩ አካላዊ እና ከአእምሮ ጉዳቶች ጋር የሚኖር በመሆኑ እንዲሁም ለአረጋውያን የሚደረገው ጥበቃ ዝቅተና በመሆኑ፤ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶችን ማስፋፋት፣ መከበር እና መጠበቃቸውን ማረጋገጥ እጅግ ከፍተኛ አስፈላጊነት እና ቅድሚያ የሚሰተው ጉዳይ ነው።
ውጤታም ምርምር እና ውትወታዎችን በማድርገ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላ ጋር አጋርነትን በማሳለጥ፤ በእነዚህ አስፈላጊ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሱ ዘርፈ ብዙ ተጋላጭነቶችን በተመለከተ ግንዛቤን ለማስፋፋት፣ ጉዳቶቹን የሀገራዊ ፖሊሲ ግንባር ቀደም አጀንዳ ለማድረግ፣ እንዲሁም አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ሰብአዊ መብቶችቻቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙ ለማስቻል ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መስፈርቶች ጋር የተጣጣመ የሕግ እና ተቋማዊ ማሻሻያ ለማድረግ እንሠራለን።