Skip to content
Facebook Twitter
  • አማርኛአማርኛ
  • EnglishEnglish
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • ስለ እኛ
    • ስለ ተቋማችን
    • ስለ ባልደረቦቻችን
    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን
  • ክልሎች
        • ክልሎች

          ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ማስከበርና መጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ራሱን የቻለ የፌዴራል ተቋም ነው።

        • አዲስ አበባ
        • አፋር
        • አማራ
        • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
        • ኦሮሚያ
        • ደቡብ ክልል
        • ሶማሌ
  • የስራ ዘርፎች
        • የስራ ዘርፎች

          እኛ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን የማስፋፋት እና የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ገለልተኛ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ነን
        • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
        • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
        • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
        • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
        • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
        • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
        • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ሪፖርት
  • ሚዲያ
    • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
    • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
    • የኢሰመኮ ጽሑፎች
  • ተጨማሪ መረጃዎች
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ሴት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ሚና እና የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች

March 18, 2022March 18, 2022 የባለሙያ አስተያየት ከኢሰመኮ

የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ሚና ያላቸው የሰብአዊ መብቶች ተቋማት እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ መረጃ የመሰብሰብ፣ የክትትል ሥራዎች እና ጥሰቶችን የማጋለጥ ሥራዎች መስራት አለባቸው።

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

Samuel Worku
Human Rights Fellow
Women’s and Children’s Rights Department, EHRC
ሳሙኤል ወርቁ
የሰብአዊ መብቶች ተባባሪ ባልደረባ
የሴቶች እና የህጻናት መብቶች ስራ ክፍል፣ ኢሰመኮ

የሰብአዊ መብቶችን የማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነት በመንግሥት ላይ የወደቀ ቢሆንም ስለ ሰብአዊ መብቶች የሚሟገቱ ግለሰቦች፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶች እና የሰብአዊ መብቶች ተቋማትም የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።  የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ጉልህ ሚና ከሚጫወቱት አካላት መካከልም ሴት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ይገኙበታል።  የአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ልዩ ዘጋቢ ሴት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች የሚለውን ሃሳብ በግልም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር ሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት እና በመጠበቅ ላይ የተሰማሩ እና በሴቶች መብቶች፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት እና በሌሎች መሰል መብቶች ላይ የሚሰሩ ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የሚያመለከት እንደሆነ ይገልጻሉ። 

ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሰብአዊ መብቶች መከበር እና መስፋፋት ከፍተኛ አስትዋጽኦ የሚያበረክቱ ሲሆን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ችግሮችን ነቅሶ የማውጣት እና የማኅበረሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ሥራዎችንም ይሠራሉ። እነዚህ ተሟጋቾች በኅብረተሰቡ ውስጥ እስከታች ወርደው የሚሠሩ በመሆናቸው በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋሉ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ጉድለቶች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ከማስቻልም አልፈው ማኅበረሰቡን እንዲሁም ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ችግሮቹ የሚፈቱበትን መንገድ በመቀየስ በኩል አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ። በተጨማሪም ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በማጋለጥ፣ ሕጎችን እና አሠራሮችን በመሞገት፣ ድህነትን እና አድሎአዊ ድርጊቶችን በመዋጋት፣ የፍትሕ ተደራሽነትን፣ ዴሞክራሲን፣ የሴቶችን እኩልነት እና ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን በማረጋገጥ በኩል ከፍተኛ አበርክቶ አላቸው። 

ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደአብዛኞቹ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሕገወጥ እስር፣ ማሰቃየት፣ ድብደባ እና እንግልት የሚጋለጡ ቢሆንም፤ ሴት በመሆናቸው ደግሞ በልዩ ሁኔታ ፆታን መሠረት ላደረጉ ድርብርብ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ ይሆናሉ። ከእነዚህም ውስጥ የኃይል ጥቃቶች፣ ትንኮሳ እና አስገድዶ መደፈርና ሌሎች ወሲባዊ ጥቃቶች፣ መገለል፣ የቃል እና የሥነ-ልቦና ጥቃቶች እንዲሁም ሰብአዊ ክብርን ለሚያዋርድ አያያዝ መጋለጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው። በአፍሪካ ያለውን የሴት ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የመብቶች ጥበቃን በሚመለከት የአፍሪካ የሰብአዊና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ይፋ ያደረገው ጥናት በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በሕይወት የመኖር፣ የአካላዊ ደህንነት የመጠበቅ፣ የነፃነት ፣ የመልክም ስም መጠበቅ፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመሰባሰብ እና የመደራጀት መብቶቻቸው እንደሚጣሱ እና ፆታን መሠረት ያደረጉ የኃይል እና የወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚፈጸምባቸው ያመላክታል። 

ይህም የዓለም ሀገራት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ያስገደደ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2014  የሴት ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጥበቃ ለማጠናከር የወጣ መግለጫ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ጸድቋል። መግለጫው በሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ለሚደርሰው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እውቅና በመስጠት ሀገራት የሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የመብቶች ጥበቃ ማዕቀፍን እንዲያጠናክሩ እና መብታቸውን ለማስከበር የሕግ፣ መዋቅራዊ/ተቋማዊ እና ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይጠይቃል። 

ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሰው በመሆናቸው ብቻ ያለምንም አድሎአዊ ልዩነት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች የተቀመጡ መብቶች ባለቤት ሲሆኑ፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ማንኛውንም አይነት አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የወጣው ዓለም አቀፍ ስምምነት አንቀፅ 7 ሀገራት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ከሚያሰናክሉ ተግባራት እንዲቆጠቡ እና ይህንን መብታቸውን እንዳይጠቀሙ እክል የሚፈጥሩ ነገሮችን እንዲያስወግዱ ያስገድዳል። 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 35 ከላይ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች የተደነገጉትን የሴቶች ሁለንታናዊ ተሳትፎ ጥበቃዎች በሚያጠናክር መልኩ ሴቶች በማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያለምንም አድሎአዊ ልዩነት ከወንዶች እኩል የመሳተፍ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል። መንግሥት እነዚህን መብቶች ትርጉም ባለው መልኩ እንዲተገበሩ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ኃላፊነት ይጥልበታል።

እ.ኤ.አ በ1981 ኢትዮጵያ ፈርማ ያጸደቀችው በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ማንኛውንም አይነት አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የወጣው ዓለም አቀፍ ስምምነት ኮሚቴ ከስምምነቱ አፈጻጸም ጋር በተገናኘ እ.ኤ.አ በ2019 ለኢትዮጵያ መንግሥት ባስተላለፈው ምክረ-ሃሳብ የኢትዮጵያ መንግሥት ሴት ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሥራቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በነፃነት ማከናወን ይችሉ ዘንድ አስፈላጊ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥበቃዎች ላይ ማሻሻያዎችን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል። 

ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሰላም እና ደህንነትን እንዲሁም ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደዱ አድሎአዊ አስተሳሰቦችን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ በመሆናቸው ሴቶችን ያላሳተፈ የሰብአዊ መብቶች ማስከበር ሂደት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። የሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የመብት ጥበቃ ማጠናከር የሰብአዊ መብት ጥበቃን በአጠቃላይ ማጠናከር በመሆኑ የሴት ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የመብት ጥበቃ ማጠናከር ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ ይገባል። በመሆኑም መንግሥት የሚያወጣቸው ሕጎች እና የሚያቋቁማቸው ተቋማት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ እና ሥርዓተ-ፆታን ያማከሉ/ያካተቱ መሆናቸውን በማረጋገጥ መሥራት ይጠበቅበታል።  በተጨማሪም በሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ አወንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ እና የመብት ጥሰቶች ተፈጽመው ሲገኙም አጥፊዎቹን ለሕግ የማቅረብ ግዴታውን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል።

የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ሚና ያላቸው የሰብአዊ መብት ተቋማት እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ መረጃ የመሰብሰብ ፣የክትትል ሥራዎች እና ጥሰቶችን የማጋለጥ ሥራዎች መስራት አለባቸው። በተጨማሪም ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ አስቻይ ሁኔታዎች መፈጠር ይችሉ ዘንድ የሕግ እና ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል የጉትጎታ/ግፊት ሥራ እና የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል።

Photo credit: Rod Waddington

Reports & Press Releases

December 10, 2021December 10, 2021 EHRC Quote
Join us and Stand Up for Human Rights on Human Rights Day
August 26, 2021February 20, 2022 ጋዜጣዊ መግለጫ
ምስራቅ ወለጋ፡ የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሊጠናከር ይገባል
June 17, 2021July 14, 2021 EHRC Quote
IPC findings underscore dismal humanitarian situation in Tigray
May 1, 2021June 4, 2021 ሪፖርት
በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቢሶበር ሲቪል ሰዎች ስለሚገኙበት ሁኔታ የተደረገ አጭር የክትትል ሪፖርት

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup

Signup for the Latest Update from EHRC

    Submit your email here to get the latest update from EHRC.

    Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

    ጠቃሚ ድረ-ገጾች

    • NANHRI
    • GANHRI
    • OHCHR
    • ACHPR

    ተሳተፉ

    • ከእኛ ጋር ለመስራት
    • አግኙን

    ከእኛ ጋር ይገናኙ

    • Facebook
    • Twitter
    • LinkedIn
    • YouTube
    EHRC
    እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን የማስተዋወቅ እና
    የማስጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠን ነፃ ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች
    ተቋም ነን
    Submit your email to get the latest update from EHRC

    © 2022 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

    ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎት ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።

    ኩኪዎችን መጠቀም ላይ መስማማትዎን እባክዎ ያሳውቁን።

    Scroll to top
    • የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)
    • ስለ እኛ
      • ስለ ተቋማችን
      • ስለ ባልደረቦቻችን
      • ከእኛ ጋር ለመስራት
      • አግኙን
    • ክልሎች
      • አዲስ አበባ
      • አፋር
      • አማራ
      • ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ
      • ሶማሌ
      • ደቡብ ክልል
      • ኦሮሚያ
    • የስራ ዘርፎች
      • የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች
      • የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች
      • የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች
      • የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች
      • የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች
      • የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
      • የሰብአዊ መብቶች ትምህርት
    • ጋዜጣዊ መግለጫ
    • ሪፖርት
    • ሚዲያ
      • ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
      • የኢሰመኮ ቪዲዮዎች
      • የኢሰመኮ ጽሑፎች
    • ተጨማሪ መረጃዎች
    • አማርኛአማርኛ
    • EnglishEnglish
    Facebook Twitter
    Search
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.