የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ
የግል አቤቱታዎች ሲደርሱን ወይም በራስ አነሳሽነት የሰብአዊ መብቶች ምርመራዎችን እናካሂዳለን፤ እንዲሁም ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መስፈርቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ እና ጥሰቶች ተገቢው ካሣ/ፍትሕ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ትክክለኛ ምርመራ እንዲደረግላቸው ለማስቻል በተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራዎች እና በብብዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ ክትትል እናደርጋለን።
ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም በኮሚሽኑ የምርመራ ሥራ መተባበር፤ እንዲሁም ኮሚሽኑ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን እና ተግባር እንዲወጣ አስፈላጊውን ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት።