የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ክሪስቲን ፒረን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሀሳብ ሀሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፣ የታዩ ዋና ዋና የለውጥ እርምጃዎችን እንዲሁም ትኩረት እና ቀጣይነት ያለው ክትትል የሚሹ አጣዳፊ ጉዳዮችን አንስተው መክረዋል።

በተጨማሪም ኢሰመኮ በሀገሪቱ አቀፍ ደረጃ የሚያካሂደውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ጥበቃ እና የማስፋፋት ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል የሚያስችሉ የጋራ ስትራቴጂካዊ የትብብር መንገዶች እና የቀጣይ አጋርነት አውዶች ላይ ተወያይተዋል።

በመጨረሻም ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ አምባሳደር ክሪስቲን ፒረን እና ልዑካናቸው ላደረጉት ገንቢ ውይይት እና ከኢሰመኮ ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ላሳዩት ቁርጠኝነት ያላቸውን ምስጋና ገልጸዋል።