ሪፖርቱ ኢሰመኮ በሪፖርት ዘመኑ ባካሄደው የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ባሰባሰበው መረጃና ማስረጃ መሠረት የተመዘገቡ አዎንታዊ እመርታዎች እና አሳሳቢነታቸው የቀጠሉ ጉዳዮችን ከምክረ ሐሳቦች ጋር ያመላክታል
መንግሥት ተገቢውን ምርመራ በማካሄድ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና ተጎጂዎችን ለመካስና ለማቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል
የምክትል ዋና ኮሚሽነር እና የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ኮሚሽነሮች መሾም፣ የአመራር ቀጣይነትን እና የተሳለጠ የሥራ ሽግግርን ከማረጋገጡም በላይ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ያለውን ዐቅም ይበልጥ ያጠናክረዋል
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል እልባት ለመስጠት የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በዞኑ በቂ የጸጥታ አካላትን ማሰማራትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ጨምሮ አፋጣኝ፣ ተጨባጭና ዘላቂ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል
በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና ልዩነቶችን በሕግ መሠረት በምክክርና በመግባባት ለመፍታት እንዲሠሩ ኢሰመኮ ያሳስባል