States Parties, as much as possible, shall prevent displacement caused by projects carried out by public or private actors
ተዋዋይ ሀገራት በተቻለ መጠን በሕዝባዊ ወይም በግል አካላት በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚፈጠርን መፈናቀል መከላከል አለባቸው
የጥቆማ መስፈርቶቹ በኢሰመኮ መቋቋሚያ አዋጅ (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት ሲሆን፣ የጥቆማ ጊዜው እስከ ዐርብ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚቆይ ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ካሉት አምስት ኮሚሽነሮች መካከል አንዷ በነበሩት የሴቶች እና ህጻናት መብቶች ዘርፍ ኃላፊ ምትክ፤ አዲስ ኮሚሽነር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሊሾም ነው። ለተተኪ ኮሚሽነርነት ዕጩ የሚሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚካሄድም ተገልጿል
Everyone charged with a criminal offence shall have the right to be presumed innocent until proven guilty according to law
በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው በሕግ አግባብ ጥፋተኝነቱ በፍርድ እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ሆኖ የመቆጠር መብት አለው
በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ለሚያድጉ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች እና እንክብካቤዎች በሕፃናት መብቶች የተቃኙ መሆን አለባቸው
The States Parties recognize the right of everyone to the enjoyment of the highest attainable standard of physical and mental health
አባል ሀገራት የማንኛውንም ሰው ሊደረስበት የሚችለውን ከፍተኛውን የአካል እና የአእምሮ ጤና ደረጃ የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተደራሽ መሆን ለአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች መከበር እና መጠበቅ ከፍተኛ ሚና አለው