በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመዋቅር እና የአስተዳደር ጥያቄዎች ለሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐስታወቀ ፡፡ በክልሉ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት በአካባቢው የፀጥታ መደፍረስን ማስከተሉን ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው የምርመራ ሪፖርቱ ዐስታውቋል
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለማችን ግጭቶች በሚደረጉባቸው አከባቢዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመቃወም በሚል የተጀመረው የፊልም ፌስቲባል ዘንድሮም ለሶስተኛ ጊዜ መደረጉን ጀምሯል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የፊልም ዐውደ ትርኢት /ፌስቲቫል/፣ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ፣ በዚኽ ሳምንት ተጀምሯል
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና የኢሰመጉ ምክትል ዋና ዲሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ በሰጡን አስተያየት፣ ለግጭቶች ብቸኛ መፍትሔ ነው ያሉት የድርድር አማራጭ፣ ተስፋ ሊቆረጥበት እንደማይገባ አመልክተዋል
በየዓመቱ ታኅሣሥ 10 የሚውለውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ለማሰብ የተጀመረው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የዘንድሮው በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት በማግኘት መብት ላይ ያተኮረ ነው
ኮሚሽኑ ከጥቅምት ወር መጨረሻ አንስቶ በክልሎቹ ውስጥ የተፈጸሙትን ጥቃቶች በተመለከተ የደረሱትን ጥቆማዎች እና አቤቱታዎችን መሠረት አድርጎ ባደረገው ክትትል፣ በሲቪል ሰዎች ላይ በተፈጸሙት ጥቃቶች ሳብያ መጠነ ሰፊ እና አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን አመልክቷል
በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ ዞን እና በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን እና በቄለም ወለጋ ዞን እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ውስጥ፣ በተፈጸሙት ጥቃቶች በቁጥር የተጠቀሱ ከ50 በላይ ሲቪሎች መገደላቸው ተገልጿል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በዐማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ ክልሎች፣ በሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ነው ያለው ጥቃት፣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ገልጿል
በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች በሲቪል ሰዎች ላይ መጠነ ሰፊና አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፤ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች እና በተከሰቱ ግጭቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ