ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ድርጊቱ በክልሉ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ምልከታ የሚጥል ነው ብለዋል
በኢትዮጵያ የተፈናቃዮችን ጉዳይ የሚከታተል ራሱን የቻለ ተቋም እና ብሔራዊ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ክፍተት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ
ኢሰመኮ ይህን የገለጸው በወቅቱ በጋምቤላ ከተማ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 18፤ 2014 ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርት ነው። ኮሚሽኑ በዚሁ ሪፖርቱ፤ ሰኔ 7፤ 2014 በጋምቤላ ከተማ የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ፤ ኢሰመኮ አንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ምርመራ ሲያደርግ እንደነበር አስታውቋል
በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በኦሮምያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች ተገለዋል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
ጥቃቱ “በኦነግ ሸኔ፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎችና ግለሰቦች በተከታታይ መፈጸሙን” ኢሰመኮ አስታውቋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ባለፈው ዓመት ባደረጉት ጣምራ ምርመራበትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ እና የጦር ወንጀል ሊባሉ የሚችሉ የወንጀል ዓይነቶች መፈፀማቸውን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መገኘታቸውን አመልክተው ነበር
ከሌሎች የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ከሕግ አግባብ ውጪ እና የመንቀሳቀስ መብታቸው ተነፍጎ፣ የሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ሁኔታ ሳይቀርብላቸው በጃሬ መጠለያ ጣቢያ ለበርካታ ወራት ተይዘው የቆዩ ናቸው ያለው ኮሚሽኑ ተፈናቃዮቹ የሚገኙበትን ሁኔታ ለመመልከት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ከመንግሥት አካላት አፋጣኝ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግሯል
ኢሰመኮ መንግስት ስላልተባበረው በአዋሽ ሰባት ያሉትን ተፈናቃዮች መጎብኘት እንዳልቻለ ገልጿል
ኢሰመኮ መንግስት ስላልተባበረው በአዋሽ ሰባት ያሉትን ተፈናቃዮች መጎብኘት እንዳልቻለ ገልጿል