To prevent harm arising from pregnancy and childbirth and in order to safeguard their health, women have the right of access to family planning education, information and capacity
ሴቶች በእርግዝና እና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከል እና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣ መረጃ እና ዐቅም የማግኘት መብት አላቸው
Everyone shall have the right to freedom of association with others, including the right to form and join trade unions for the protection of his interests
ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በማኅበር የመደራጀት ነጻነት አለው፡፡ ይህም ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ የሠራተኛ ማኅበራትን የማቋቋም እና አባል የመሆን መብትን ይጨምራል
A child temporarily or permanently deprived of his or her family environment, or in whose own best interests cannot be allowed to remain in that environment, shall be entitled to special protection and assistance provided by the State
ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው
Accused persons have the right to be informed with sufficient particulars of the charge brought against them and to be given the charge in writing
የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸው ክስ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገራቸው እና ክሱን በጽሑፍ የማግኘት መብት አላቸው
Women have the right to a peaceful existence and the right to participate in the promotion and maintenance of peace
ሴቶች በሰላም የመኖር እንዲሁም ሰላምን በማስፋፋትና በማስጠበቅ ሥራዎች ላይ የመሳተፍ መብት አላቸው