በሀገር ውስጥ በሴቶች እና በሕፃናት የመነገድ ድርጊትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉን አቀፍ ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ማኅበራዊ ስልቶች ሊነደፉ ይገባል
በኢትዮጵያ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋል
መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
በሕግ፣ በፖሊሲና በአሠራር ረገድ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ለሴቶች እና ለሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ይገባል
ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍ በ2016 ዓ.ም. የተሻለ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዘርፍ ሲሆን፤ የፖሊሲና የሕግ ማሻሻያን ጨምሮ ጠንካራ የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል
አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ቦታዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች ውጭ አጠቃላይ ሕዝበ ውሳኔው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎላ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጻ የነበረ ነው
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሥር መንስኤ የሆኑ የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት ያሻል (የ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት)
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበት
የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል