አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ቦታዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች ውጭ አጠቃላይ ሕዝበ ውሳኔው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎላ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጻ የነበረ ነው
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሥር መንስኤ የሆኑ የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት ያሻል (የ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት)
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበት
የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነጻ መሆን አለባቸው
የአተገባበር ክትትል በተሠራበት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሌ ክልል የተለዩ ቦታዎች ዝናብ መዝነቡ የድርቁ አደጋ ማብቂያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም
ማእከላቱ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መመዘኛዎች፣ የተ.መ.ድ. የአረጋውያን መርሆችና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣውን አነስተኛ መስፈርት በማሟላት የአገልግሎቶቻቸውን ጥራት ለማሻሻል እና ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ መንግሥት ድጋፍ በማድረግ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል
የተሟላ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ወይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንዲሻሻል ያስፈልጋል
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ ይገባል