ክትትሉ በዋናነት ያተኮረው በማእከላቱ አደረጃጀት፣ በተጠቃሚዎች ልየታ ሥርዓት፣ በአገልግሎት ዓይነቶች እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ሲሆን፤ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሕጎች እና መርሆች አንጻር በመገምገም ምክረ ሐሳቦችን ይሰጣል፡፡ በዚህ ክፍል የክትትሉ አንኳር ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ አረጋውያን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው ለሚመጡ አድሎዎች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ በመሆናቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት ሲባል አረጋውያንን በአንድ ማእከል ውስጥ አሰባስቦ እንክብካቤ መስጠት...
This Advisory Note on Transitional Justice prepared by the Ethiopian Human Rights Commission and the United Nations Office of the High Commissioner for Human Rights presents the preliminary findings of thirteen community consultations held on transitional justice with over 700 individuals in several regions of Ethiopia, between July and December 2022. In addition to presenting...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፤ የመፈናቀሉ አውድ እና መንስኤዎች፣ በመፈናቀል ወቅት ያጋጠሙ አንኳር የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክፍተቶች እና የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶችን ለመለየት ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች (ደ/ብ/ብ/ሕ) ክልል በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ...
ይህ ዓመታዊ የሴቶችና የሕፃናት መብቶች የዘርፍ ሪፖርት ከመስከረም 2014 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2014 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን ኢሰመኮ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሃሳቦችን አካቷል፡፡ ኮሚሽኑ...
(Download the English version below) ⬇️ ይህ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ በሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ባለፈው የበጀት ዓመት ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ...
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established as per the Federal Constitution and reporting to House of People’s Representatives as a national human rights institution with the mandate for promotion and protection of human rights. (Article 55/14 of FDRE Constitution cum Proclamation No. 210/2000, as amended by Proclamation No.1224/2020).
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌደራል ሕገ-መንግሥቱ መሠረት ነጻ ፌደራላዊ መንግሥት አካል ሆኖ የተቋቋመና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበርና እና ጥበቃ የሚሠራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ነው፡፡ (የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55/14 እና አዋጅ ቁጥር 210/1992 በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው፡፡)
የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ እና ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና ግልጋሎት እና በመጠለያ መብቶች ረገድ ያለውን ክፍተት በመለየት መብቶቹን ለማሟላት ተገቢውን እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እና በመንግሥትና በአጋር ድርጅቶች ለድርቁ የሚሰጡ ምላሾች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ፤ ቁጥር ፪፻፲/፲፱፻፺፪ (በአዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፳፬/፪ሺ፲፪ እንደተሻሻለው) Federal Democratic Republic of EthiopiaEthiopian Human Rights Commission Establishment Proclamation (AsAmended)Proclamation No. 210/2000(As Amended by Proclamation No. 1224/2020)