(Download the English version below) ⬇️ ይህ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ በሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ባለፈው የበጀት ዓመት ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ...
የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ እና ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና ግልጋሎት እና በመጠለያ መብቶች ረገድ ያለውን ክፍተት በመለየት መብቶቹን ለማሟላት ተገቢውን እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እና በመንግሥትና በአጋር ድርጅቶች ለድርቁ የሚሰጡ ምላሾች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) መካከል የተደረገው ውጊያን ተከትሎ ከሰኔ 7 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ታጣቂ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ የንብረት ጉዳት...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ሪፖርት።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ሪፖርት። የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች (Executive Summary) እዚህ ተያይዟል
ይህ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ የሥራ ክፍሎቹ እና ጽ/ቤቶቹ አማካኝነት ባደረገው ክትትልና ምርመራ፣ ባከናወናቸው መለስተኛ ጥናቶች፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ባካሄዳቸው ምርመራዎች፣ በውትወታ እና በሌሎች ተግባራቶቹ አማካኝነት ከተገኙ መረጃዎች የተዘጋጀ ነው። ሙሉ ሪፖርቱ...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ ባሰማራው የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ቡድንና ተከታታይ የምርመራ ስልቶች በአፋርና አማራ ክልሎች ተስፋፍቶ በቆየው ጦርነት የተከሰቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን መርምሯል፡፡ ⬇️ ሙሉ ሪፖርቱ ያለ አባሪዎቹ ⬇️ የሪፖርቱ አባሪዎች ⬇️ የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች ⬇️ Executive Summary
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት አርዳ ጅላ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሕይወትና የአካል ጉዳት ስለመፈጸሙ በደረሰው ጥቆማ መሰረት፣ ከታኅሣሥ 7 እስከ ታኅሣሥ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት ምርመራ አካሂዷል።
ኢሰመኮ በደረሱት መረጃዎች መነሻነት በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአንዳንድ የትግራይ ክልል ደቡባዊ አካባቢዎች በጦርነት አውድ ውስጥ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ከነሐሴ 22 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ምርመራ አካሂዷል። ይህ ሪፖርት የዚህ ምርመራ ውጤት ነው።