- Version
- Download 205
- File Size 787.31 KB
- File Count 1
- Create Date November 11, 2022
- Last Updated November 11, 2022
የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር ክትትል ሪፖርት – “የዛፍ ላይ እንቅልፍ ”
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሠራተኞች ላይ የተሠሩ ጥናቶችን እና የቀረቡለትን በርካታ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ባለ 58 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። በክትትል ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሠሩ በተለይም በሃዋሳ፣ ባሕር ዳር፣ አዲስ አበባ እና ጅማ ከተሞች፤ በአጠቃላይ 122 ሠራተኞች (83 ወንድ እና 39 ሴት)፣ 18 የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች፣ 25 ተጠቃሚ ድርጅቶች፣ 19 አግባብነት ያላቸው የመንግሥት ኃላፊዎች፣ 10 ሌሎች ባለድርሻ አካላት እና 6 የሠራተኞች ማኅበራት አመራሮችን በማሳተፍ መረጃዎች ተሰብስበዋል።
⬇️ የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር ክትትል ሪፖርት አባሪዎች