በሰው የመነገድ ወንጀል ማለት ግለሰቦችን ለብዝበዛ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማታለል ወይም በኃይል በመመልመል፣ በማጓጓዝ፣ በማሸጋገር፣ በመቀበል፣ ወይም በማስጠለል የሚፈጸም ድርጊት ነው
ኢሰመኮ ቀዳሚው ትኩረት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋነኛ ምክንያት የሆኑ የሥር መንስኤዎችን ለመፍታት ሊሆን እንደሚገባ አሳሰበ
Every individual shall have the right to have his cause heard
ማንም ሰው በደሉ እንዲሰማለት የማድረግ መብት አለው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩ ፈንጂዎችን የማጽዳቱ ሥራ በአስቸኳይ መጠናቀቅ እንደሚኖርበት አሳስቧል
በሰው የመነገድ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ
መንግሥት ለፈንጂ ተጎጂዎች (Landmine victims) የማቋቋም እና የተሐድሶ አገልግሎት ድጋፎችን ማቅረብ አለበት
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ በሀገራችን ባለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ የተሻሻሉ ጉዳዮች ቢኖሩም እየተባባሱ የመጡ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በስፋት ይስተዋላሉ
ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ የስትራቴጂ ዕቅድ ጸድቆ ወደ ሥራ ሲገባ የጥበቃና ድጋፍ ሥርዓት እንደሚዘረጋ ይጠበቃል
ከዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች ስምምነት ጋር የተጣጣመ ረቂቅ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች አዋጅ እንዲዘጋጅ፣ እንዲጸድቅ እና ወደ ሥራ እንዲገባ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ አለባቸው