አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነጻ መሆን አለባቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ያላቸውን የተደራሽነት እና አካታችነት ሁኔታ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ተማሪ የሆነው ቢኒያም ኢሳያስ ያቀረበውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል ባለ 30 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ክትትሉ ከነሐሴ 10 እስከ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በጎንደር፣ ሐረማያ፣ ሃዋሳ...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ፤ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ የአካል ጉዳተኞች የከፍተኛ ትምህርት ተካታችነትን ሁኔታ ለመፈተሽ ያስችለው ዘንድ የኢትዮጵያ የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች እንዲሁም አጠቃላይ ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣ የመረጃ እና የአመለካከት ተደራሽነትን...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአገሪቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቀ
“መንግሥት የአስገድዶ መሰወር ወንጀል ሰለባ ለሆኑ ሰዎች መፍትሔ መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህንን ወንጀል ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ እንድታጸድቅ ጥሪ እናቀርባለን” - የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ጉዳይ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል
የአስገድዶ መሰወር ወንጀልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ ልታጸድቅ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ ከሚገኙ በተለይ በኤርትራዊያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በቀረቡ አቤቱታዎች መሠረት ክትትል ማድረጉን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል
ለችግሩ እልባት የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የምዝገባ አገልግሎት እና የመታወቂያ ሰነድ እድሳት በአፋጣኝ መጀመር አለበት