በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆምና የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ ይገባል
A child temporarily or permanently deprived of his or her family environment, or in whose own best interests cannot be allowed to remain in that environment, shall be entitled to special protection and assistance provided by the State
ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከ2014 ዓ.ም. እስከ 2015 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው ግኝቱ የማረሚያ ተቋማትን ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመላክቷል
ከንግድ ጋር የተያያዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመከላከል ያለመ ብሔራዊ የድርጊት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል
Accused persons have the right to be informed with sufficient particulars of the charge brought against them and to be given the charge in writing
የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸው ክስ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገራቸው እና ክሱን በጽሑፍ የማግኘት መብት አላቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፍሬድሪክ ኤልበርት ስቲፍታንግ (Friedrich Elbert Stiftung) ጋር በመተባበር የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ዝግጅት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፤ ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት የሰጠ የንግድና የልማት አሠራርን ማስቀጠል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም የመንግሥት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎችም ቅንጅታዊ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል
ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው