ኮሚሽኑ ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30/ 2016 ዓ.ም ድረስ አከናውኘዋለሁ ባለው ምርመራ ግጭቶቹ በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላና ጉግ ወረዳዎች እንዲሁም በክልሉ ዋና ከተማ ጋምቤላ ተከስተዋል ብሏል
በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በተካሄዱ ግጭቶች፤ ቢያንስ 138 ሰዎች መገደላቸውን እና በ113 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በግጭቶቹ የተነሳ በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን፣ መኖሪያ ቤቶች እና ንብረቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም ዘረፋ መፈጸሙን ኮሚሽኑ ገልጿል
የጥፋተኞችን ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የማኅበረሰብ ውይይቶች፣ የሰላምና ዕርቅ ተጨባጭ እርምጃዎች ለዘላቂ መፍትሔ አስፈላጊ ናቸው
በጋምቤላ ክልል የቤተሰብ ሕግ አፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን በሚገባ ለመመለስ ሕጉ የማኅበረሰቡን ወግ፣ ባህል፣ እሴቶች እና የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም ኅብረተሰቡ አሁን ያለበትን የእድገት ደረጃ ያማከለ ሆኖ መሻሻል ያስፈልገዋል
በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች የሚያስፈልጓቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት እንቅፋት የሆኑ ችግሮች መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን ይገባል
ኮሚሽኑ በቅርብ ጊዜ አደርግሁት ባለው ክትትል "በስደተኞች ሠፈሮች ውስጥ የከፋ ሰብአዊ ሁኔታ እና የምግብ አቅርቦት እጥረት እየጨመረ መምጣቱን አሳሳቢ ብሎታል። የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የርዳታ ድርጅቶች ለስደተኞች ይሰጡት የነበረዉን ሰብአዊ ርዳታ ማቋረጣቸዉን አስታዉቋል
“በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች ለከፋ ረኀብ ተጋልጠዋል” - ኢሰመኮ
EHRC Director of Law and Policy Tarikua Getachew speaks with Omny Studio
በጋምቤላ ክልል ከ30 ያላነሱ ስደተኞች በረሃብና በምግብ እጦት እንዲሁም ምግብ ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ በደረሰባቸው ጥቃት መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ