ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከነበራቸው ተሳትፎ፣ ተደራሽነት እና አካታችነት አንጻር የተስተዋሉ ክፍተቶችን መለየት ለቀጠይ ምርጫ መሻሻል መሰረት ነው
ኢሰመኮ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በኮንሶ ዞን፣ በአሌ፣ በደራሼና አማሮ ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ያገኙ ዘንድ በትብብር እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፤ የመፈናቀሉ አውድ እና መንስኤዎች፣ በመፈናቀል ወቅት ያጋጠሙ አንኳር የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክፍተቶች እና የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶችን ለመለየት ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች (ደ/ብ/ብ/ሕ) ክልል በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ...
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 50 ገጽ ሪፖርት ባለፈው ሐምሌ 19/2014 ይፋ አድርጓል
የብሔራዊ ምርመራ ህዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ ዘዴን ማካሄድ የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በግጭቶች የተጎዱ ሰዎችና አካባቢዎችንም መልሶ ለመጠገን እና ለማቋቋም በቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ያስፈልጋል
በደቡብ ክልል “የበዙ” ያላቸው የመብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ጥሰቶቹ የሚፈፀሙት ከወሰን እና ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያያዙ ምክንያቶችና ከህግ ክፍተትና አሠራር ግድፈት የተነሳ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል
የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶችን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ላይ በአትኩሮት መሥራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው