በ2016 ዓ.ም. በበርካታ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተለምዶ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያቶች ሳቢያ ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው 3ኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ወደሚገኝ “መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ” የተወሰዱ እስረኞች ብዛት 53 መሆናቸውን አስታውቆ ነበር
የቅድመ ክስ እሥርን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት እንዲሁም የፍትሐዊ እና ሰብአዊ መብቶች መርኾችን ያካተተ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት፤ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች የሚጣሱባቸውን ዐውዶች በመመርመር፣ የጥሰት መንስኤዎችን እልባት ለመስጠት፣ ጥሰቶችን ለማስቆም፣ በጥሰቶች ተሳታፊ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እና ለተጎጂዎች ተገቢ የሆነውን የካሳ ሥርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ይህንኑ በሥራ ላይ ለማዋል የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል” ብለዋል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለአምስት ዓመታት በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና የቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ያካሄደውን የዜጎች ነጻነት የተመለከተ ብሔራዊ ምርመራ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም. ባሉት አምስት ዓመታት ነጻነታቸውን በተነፈጉ ሰዎች መብቶች ዙሪያ በአራት ክልሎች ባከናወናቸው 4 ብሔራዊ ምርመራ /National Inquiry/ የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን ያጠናቀረ ባለ 130 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል
የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማስቆም፣ በጥሰቶች ተሳታፊ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እና ለተጎጂዎች ተገቢ የሆነውን የካሳ ሥርዓት ለመዘርጋት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል
ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአስገዳጅ ሁኔታ ከጎዳና ላይ እያፈሱ ወደ ሌላ ቦታ የመውሰዱ አሰራር በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ የሰዎች ማቆያ ስፍራ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። የኦሮሚያ ክልል በበኩሉ በክልሉ የሰዎች ማቆያ ስፍራ አለመኖሩን ይገልጻል