የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን ያልተከተሉ እስሮች በአፋጣኝ እንዲቆሙ ጠየቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትጥቅ ግጭት እና በጸጥታ መደፍረስ ወቅትም ቢሆን ሲቪል ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያበቃ በቂ ሕጋዊ ምክንያት መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብሏል
ኢሰመኮ በዚህ መግለጫው፤ “ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ” እስር ተፈጽሞባቸዋል ካላቸው ውስጥ የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሚዲያ እና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ይገኙባቸዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ መልክ ጎንደር እና ባሕር ዳር ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚፈጸመውን የበርካታ ሰዎች እስር በተመለከተ ክትትል ማድረጉን የሚቀጥል ሲሆን፣ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል የሚገባ መሆኑን ያሳስባል
በትጥቅ ግጭት እና በጸጥታ መደፍረስ ወቅትም ቢሆን ሲቪል ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያበቃ በቂ ሕጋዊ ምክንያት መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
ከኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር የተደረገ ቆይታ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች በአሳሳቢ ሁኔታ መባባሳቸውን አስታውቆ መንግሥት ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠየቀ
ኮሚሽኑ በለቀቀው መግለጫ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ካለው የትጥቅ ችግር ጋር በተያያዘ በአንዳንድ አካባቢዎች የሕግ ማስከበሩ በመላላቱ ሰላማዊ ዜጎች በታጣቂዎች፣ በተደራጁ ቡድኖች እና በአንዳንድ የመንግሥት የፀጥታ አካላት የሚደርስባቸው እገታ ተባብሷል ብሏል
ወንጀሉ በአብዛኛው እንደ ገቢ ማስገኛ የተወሰደ መሆኑን የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ድርጊቱ "በተደጋጋሚ፣ በተንሰራፋና በተደራጀ መልኩ እንደሚፈጸም፤ አልፎ አልፎም እንደ በቀል፣ ለፖለቲካ ዓላማ ወይም የታገተ ሌላ ሰውን ለማስለቀቅ በሚል በአጸፋ መልኩ የሚፈጸም መሆኑን" ስለመረዳቱ አመልክቷል
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለውን የእገታ ተግባር ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስቆም ለሰዎች እገታ መነሻና አባባሽ ምክንያት የሆነውን የሰላም መደፍረስና የትጥቅ ግጭትን በዘላቂነት በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ጨምሮ ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው