የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ም/ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዋና ኮሚሽነሩ ዳንዔል በቀለን ጨምሮ አምስት የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘቱን አስመልክቶ ዛሬ ነሐሴ 27 ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ ላይ ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዋሽ አርባ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በእሥር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን መጎብኘቱን ትናንት ቅዳሜ ነሐሴ 27 ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉትን የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ሌሎች እስረኞችን መጎብኘቱን ገለጸ