ኮሚሽኑ ይህንን እገዳ ተከትሎ የደረሱትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችን ማነጋገሩን ገልጿል
ኢሰመኮ በተሸርካሪዎቹ ላይ የተጣለው እግድ እንዲነሳ የጠየቀው ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 7፤ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ ኮሚሽኑ፤ አንድ ሳምንት የሆነው የከተማ አስተዳደሩ እግድ መግለጫውን እስከወጣበት ጊዜ ድረስ አለመነሳቱ እንዳሳሰበው አስታውቋል
በጠቅላላ ከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶች አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው