የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር መዘጋጀት የንግድ ተቋማት ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ያስችላቸዋል
ከንግድ ጋር የተያያዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመከላከል ያለመ ብሔራዊ የድርጊት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፍሬድሪክ ኤልበርት ስቲፍታንግ (Friedrich Elbert Stiftung) ጋር በመተባበር የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ዝግጅት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፤ ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት የሰጠ የንግድና የልማት አሠራርን ማስቀጠል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም የመንግሥት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎችም ቅንጅታዊ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል
Businesses must find the proper balance between enabling the realization of human rights and avoiding causing human rights abuses
የንግድ ሥራዎች በአግባቡ መመራታቸው ለሰብአዊ መብቶች መተግበር አወንታዊ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ያስችላል
የንግድ ተግባራት በአግባቡ ካልተመሩ የጤና፣ የመኖሪያ ቤት፣ የምግብ፣ ውሃ፣ ማኅበራዊ ደኅንነት፣ የመሥራት መብት፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ የማግኘት እንዲሁም የንግድ ማኅበራትን የመመሥረትና የመቀላቀል መብቶች አተገባበር ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ