የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሚታሰሩ መሆናቸውን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገልጿል
በሀገሪቱ በተከሰቱ ሰው ሠራሽ ቀውሶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶችና ሕፃናትን ለመፈናቀል፣ ለጾታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም ለሌሎች ተደራራቢ የመብት ጥሰቶች ተጋላጭነታቸውን እንደጨመረ በሪፖርቱ ገልጿል
በሕግ፣ በፖሊሲና በአሠራር ረገድ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ለሴቶች እና ለሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ይገባል
ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሐሳቦችን አካቷል
ማንኛውም አእምሮው ወይም አካሉ የተጎዳ ሕፃን ከመንፈሳዊና ከአካላዊ ፍላጐቱ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ክብሩን የሚያረጋግጥ፣ በራስ መተማመኑንና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የሚያሳድግ የተለየ የጥበቃ እርምጃ ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው
A child who is mentally or physically disabled shall have the right to special measures of protection in keeping with his physical and moral needs and under conditions which ensure his dignity and promote his self-reliance and active participation in the community
ወጣት አጥፊዎች በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች ከአዋቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው
Juvenile offenders admitted to corrective or rehabilitative institutions shall be kept separate from adults
መከላከልን መሠረት ያደረገ ለሕፃናት ከፍተኛ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ የመብት ጥበቃ ተግባራዊ እንዲደረግ የባለድርሻ አካላትን ትኩረት ይሻል
ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው