በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ያስፈልጋል
የጤና መብት እና የግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር ክትትል ሪፖርቶችን መሠረት ያደረጉ የውትወታ መድረኮች ተካሄዱ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሚታሰሩ መሆናቸውን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገልጿል
በሀገሪቱ በተከሰቱ ሰው ሠራሽ ቀውሶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶችና ሕፃናትን ለመፈናቀል፣ ለጾታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም ለሌሎች ተደራራቢ የመብት ጥሰቶች ተጋላጭነታቸውን እንደጨመረ በሪፖርቱ ገልጿል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን “በወንጀል የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ሕፃናት አያያዝ በማንኛውም ሁኔታ እና ወቅት ዓለም አቀፍና ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን በማሟላት እንዲተገበሩ” ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ “ከእስረኛ እናታቸው ጋር ማረሚያ ቤት ለሚቆዩ ሕፃናት አማራጭ የእንክብካቤ ማዕቀፍ” ሊመቻች እንደሚገባ ማሳሰቢያ ሰጥቷል
በሕግ፣ በፖሊሲና በአሠራር ረገድ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ለሴቶች እና ለሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ይገባል
ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሐሳቦችን አካቷል