ለእናቶችና ለጨቅላ ሕፃናት የጤና መብቶች ጥበቃ ተግዳሮት የሆኑ የጸጥታ እና የመሠረተ ልማት ችግሮች የመንግሥትን አፋጣኝ ምላሽ ይሻሉ
የእናቶች እና የጨቅላ ሕፃናትን የጤና መብቶች ሁኔታን ለማሻሻል መንግሥትን ጨምሮ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት አስፈላጊ ነው
በመግለጫው ዙርያ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ በኮሚሽኑ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶር. አብዲ ጅብሪል፣ ተቋማቸው፥ በዘርፉ፣ ከተደራሽነት አኳያ ክትትል ማድረጉን ጠቅሰው፣ የግል የጤና ተቋማት፣ በክፍያ መወደድ ምክንያት፣ ለኅብረተሰቡ በሚፈለገው ደረጃ ተደራሽ እንዳልኾኑ አረጋግጠናል፤ ብለዋል
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአብዛኛው በመንግሥት ሲቀርብ በነበረው የጤና አገልግሎት ላይ የግሉ ዘርፍ በሰፊው መሰማራቱ ሊበረታታ እንደሚገባው ገልጸው፣ ተቋማቱ ካላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት አንጻር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ አስታውቀዋል
የግሉ የጤና ዘርፍ አገልግሎት ከመንግሥት የጤና ዘርፍ አገልግሎት አንጻር ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል
የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል