የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህንን የተናገረው ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ድረስ የነበረውን ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርትን ሀምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው
በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ችግሮቹን የሚመጥን የመፍትሔ እርምጃ እየተወሰደ አይደለም ተብሏል
ኢሰመኮ ቀዳሚው ትኩረት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋነኛ ምክንያት የሆኑ የሥር መንስኤዎችን ለመፍታት ሊሆን እንደሚገባ አሳሰበ
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሥር መንስኤ የሆኑ የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት ያሻል (የ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት)
ስልጠናዎቹ በአካል ጉዳተኞች፣ በሕፃናት፣ እንዲሁም በሕግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው
የሦስትዮሽ ትብብሩ የመብት ተሟጋቾች ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና እና እንግልት በጋራ ለመከላከል እና ለመቋቋም ትልቅ ሚና ይኖረዋል
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበትም ብሏል ኢሰመኮ
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበት
Every individual shall have the right to the respect of the dignity inherent in a human being and to recognition of his legal status
ማንኛውም ግለሰብ ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰው ልጅ ክብር የማግኘት እና በሕግ ፊትም ዕውቅና የማግኘት መብት አለው