የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማስቆም፣ በጥሰቶች ተሳታፊ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እና ለተጎጂዎች ተገቢ የሆነውን የካሳ ሥርዓት ለመዘርጋት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል
The Ethiopian Human Rights Commission has called for an end to what it calls a rising trend of enforced disappearances in the country
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ የዮናስ ብርሃነን መታሰር አስመልክተው፣ ትላንት ሰኔ አራት ቀን፣ በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ድርጊቱ ሕገ ወጥ እና ተቀባይነት የሌለው ነው፤” ሲሉ ኮንነዋል
የኢትዮጵያ ስብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣ ነው ባለው እና በመንግስት የጸጥታ ኃይላት የሚፈጸም ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል
በኢትዮጵያ፣ በመንግሥት አካል ወይም በአካሉ እውቅና የሰዎችን ደብዛ የማጥፋት ድርጊት መጨመሩን ያስታወቀው ኢሰመኮ፣ በአፋጣኝ መቆም እንዳለበት አሳሰበ
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) «የተሰወሩ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ፣ በተሰወሩበት ጊዜ ሁሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ» አሳስበዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመንግሥት የፀጥታ አካላት በማንኛውም ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ ሠልፎች እንዲሁም ሌሎች ስብስባዎች፣ ተመጣጣኝ ካልሆነና ሞት ከሚያስከትል የኃይል ዕርምጃ መውሰድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአገሪቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቀ
“መንግሥት የአስገድዶ መሰወር ወንጀል ሰለባ ለሆኑ ሰዎች መፍትሔ መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህንን ወንጀል ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ እንድታጸድቅ ጥሪ እናቀርባለን” - የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ