ዘላቂ መፍትሔ እስኪረጋገጥ ድረስ ተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሆነ የሰብአዊ ድጋፍ ሊቀርብላቸው እንዲሁም በቂ መጠለያ ሊመቻችላቸው ይገባል
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች፥ በቂ፣ ተደራሽ እና ወቅቱን የጠበቀ የምግብ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የተሟላ እና በቂ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቢኖርም፣ ባለፉት ወራት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች ትኩረት በመስጠት በሁለት ዙር ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል ተብሏል
የተፈናቀሉ ሰዎች ከመንግሥት አካላት ጥበቃ እና ሰብአዊ ድጋፍ የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አላቸው። ይህን ጥያቄ በማቅረባቸው ሊከሰሱ ወይም ሊቀጡ አይገባም
መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው