የመንግሥት የጸጥታ አካላት አላስፈላጊና ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል የመጠቀም አዝማሚያ እየጨመረ መምጣቱን እና በዚህም ሳቢያ በሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት እንዲሁም ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየደረሱ ናቸው
ባለፈው ሳምንት በአንዋር መስጂድ የሞቱና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በተመለከተ መንግስት ጉዳቱን የሚያጣራ ቡድን ማቋቋሙንም አረጋግጫለሁ ብሏል በመግለጫው
"ለሰው ሕይወት እልፈትና አካል ጉዳት ተጠያቂ የሆኑ የጸጥታ አካላት ተለይተው በሕግ እንዲጠየቁ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ወንጀል ስለመፈጸማቸው በቂ ጥርጣሬ ከሌለ እና ተዓማኒ ክስ የማይቀርብ ከሆነ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ወይም በሕግ አግባብ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች የዋስትና መብት ሊከበር ይገባል" የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ሰላማዊ በሆኑ ሃይማኖታዊ ስብስቦች ወቅት የሚወሰድ እርምጃ በተለይም የመንግሥት የጸጥታ አካላትን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን