ኢሰመኮ አቤቱታ አቅራቢዎች እና የመንግስት አካላት ፊት ለፊት ቀርበው የተከራከሩበት ግልጽ ምርመራ በአዳማ አካሂዷል
የግልጽ የምርመራ መድረኩ ተጎጂዎች፣ ባለግዴታዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እልባት ለማስገኘት እና አስቀድሞ ለመከላከል የመፍትሔ ሐሳቦችን ያመላከተ ነው
የብሔራዊ ምርመራ ህዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ ዘዴን ማካሄድ የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ብሔራዊ ምርመራ ውስብስብና ተደጋጋሚ የሆኑ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በበርካታ አካባቢዎች የሚታዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በጥልቀት ለመመርመር እና ስልታዊና ዘርፈ ብዙ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ የሚጠቅም ዘዴ ነው
በደቡብ ክልል “የበዙ” ያላቸው የመብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ጥሰቶቹ የሚፈፀሙት ከወሰን እና ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያያዙ ምክንያቶችና ከህግ ክፍተትና አሠራር ግድፈት የተነሳ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል