የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 138 ሰዎች ህይወት አልፏል ብሏል
በኦሮሚያ ግጭት የሚሳተፉ ሁሉም አካላት “ሲቪል ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ እና በተስፋፋ ሁኔታ ከሕግ ውጪ ግድያዎችን” መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል
በኦሮሚያ ክልል ባላፉት ሁለት አመታት የመንግሥት እና የታጣቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ ባደረሱት እጅግ በርካታ ከሕግ ውጪ ጥቃቶች “እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት” (grave violation of human rights) ፈጽመዋል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
A new report from the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) reveals extrajudicial killings and civilian deaths in Oromia have grown increasingly alarming
በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎችንና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ማቆም፣ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ ተጎጂዎችን መካስ እና ለዘላቂ መፍትሔ በሁሉም ወገኖች ሰላማዊ ውይይትን በቁርጠኝነት መቀበል ይገባል
ኮሚሽኑ የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ያደረገው በክልሉ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ እና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች ላይ አተኩሮ መሆኑን ባወጣው ምግለጫ ጠቅሷል
ኮሚሽኑ ከጥቅምት ወር መጨረሻ አንስቶ በክልሎቹ ውስጥ የተፈጸሙትን ጥቃቶች በተመለከተ የደረሱትን ጥቆማዎች እና አቤቱታዎችን መሠረት አድርጎ ባደረገው ክትትል፣ በሲቪል ሰዎች ላይ በተፈጸሙት ጥቃቶች ሳብያ መጠነ ሰፊ እና አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን አመልክቷል
የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት በሕፃናት መሠረታዊ መብቶች የተቃኙ የእንክብካቤ፣ አገልግሎቶችና የጥበቃ ሥርዓቶች ሊኖራቸው ይገባል
ኢሰመኮ አነጋገርኳቸዉ ያላቸዉ የመንግስት ባለስልጣናት የማቆያ ጣቢያዉ ዓላማ «ከየጎዳናዉ የተነሱት ሰዎች በመልሶ ማቋቋም መርሐ-ግብር መሠረት ወደየመጡበት እንዲመለሱ ለማገዝ ነዉ» ማለታቸዉን ኮሚሽኑ ጠቅሷል
የጎዳና ተዳዳሪዎችን በግዳጅ ማቆያ ማዕከላት እንዲገቡ የማድረግ ተግባር በአፋጣኝ እንዲቆምና ለዚሁ ለችግር ዘለቄታዊና ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ