በማቆያዎች እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን መጨናነቅ እና አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል አማራጭ ቅጣቶችን ጨምሮ ሌሎች የፖሊሲ አማራጮችን መተግበር ይጠይቃል
በጾታ የተለየ ማደሪያ ክፍል እና ለሴቶች ቅድሚያ የሚሰጥ አሠራር አለመኖር ሴት ተጠርጣሪዎችን እና ታራሚዎችን ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያጋልጣል
የተጠርጣሪዎችን ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል የተጠያቂነት ሥርዓትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው
መንግሥት በታራሚዎች ላይ የሚፈጸም ድብደባን በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ሊያርም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
በማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎችም ሆኑ በፖሊስ ጣቢያዎች ያሉ ተጠርጣሪዎች ኢሰብአዊ ከሆነ አያያዝ ሊጠበቁ ይገባል