መንግሥት የታራሚዎችን ሰብአዊ መብቶች በማክበር፣ በማስከበር እና በማሟላት ረገድ ቀዳሚ ኃላፊነት አለበት
የኦሮምያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከሕግ አግባብ ውጭ የሚፈፀሙ እሥራቶችና የተያዙ ሰዎችን መብቶች የሚጥሱ አሠራሮችን መመልከቱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል
ኮሚሽኑ በ126 ፖሊስ ጣቢያዎች ባደረገው ክትትል፣ ታሳሪዎች የታሰሩበትን ምክንያት አለመንገር፣ ሰዎችን በአስተዳደር አካላት ትዕዛዝ ብቻ ማሰር፣ ዋስትና የተፈቀደላቸውን ሰዎች አስሮ ማቆየት፣ ባልተያዙ የወንጀል ተጠርጣሪዎች ምትክ ቤተሰቦቻቸውን ማሰር፣ ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ወንጀል እንዲያምኑ መደብደብና ምግብ፣ መጠጥ ውሃና ሕክምና አለመስጠት በስፋት መመልከቱን ገልጧል
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተስተዋሉበት ወቅት በፍጥነት እንዲስተካከሉና መሻሻል እንዲመጣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ፤ የመንግሥት አካላትን በተደጋጋሚ መወትወታቸውን ያስረዳሉ