ኢሰመኮ አቤቱታ አቅራቢዎች እና የመንግስት አካላት ፊት ለፊት ቀርበው የተከራከሩበት ግልጽ ምርመራ በአዳማ አካሂዷል
የግልጽ የምርመራ መድረኩ ተጎጂዎች፣ ባለግዴታዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እልባት ለማስገኘት እና አስቀድሞ ለመከላከል የመፍትሔ ሐሳቦችን ያመላከተ ነው
የብሔራዊ ምርመራ/ግልጽ ምርመራ በሕዝብ ፊት የሚካሄዱ የአቤቱታ መቀበያ መድረኮቹን ተከትሎ ግኝቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን የያዘ ሪፖርት ይፋ የሚደረግ ይሆናል