በጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደው ይህ ሕዝበ ውሳኔ ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው 186 ጣቢያዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች (minor electoral irregularities) ውጪ፤ አጠቃላይ ምርጫው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ነጻ የነበረ ነው