የኦሞ ወንዝን በከፍተኛ ሁኔታ መሙላት እና የዳሰነች ወረዳ በርካታ አካባቢዎችን በጎርፍ መጥለቅለቅ ተከትሎ፣ ሰዎች ለመፈናቀል ከመዳረጋቸው ባሻገር፣ በሕይወታቸው፣ በአካላቸው፣ በንብረታቸው እንዲሁም ትምህርት እና ጤናን ጨምሮ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በሚያገኙባቸው ተቋሟት ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑን የክትትል ሪፖርቱ ያመለክታል
በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ለሚከሰቱ መፈናቀሎች የሰብአዊ መብቶች መርሖችን የተከተለ ዘላቂ መፍትሔ ማመቻቸት ይገባል
ረቡዕ ግንቦት 14 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ኦሞ ዞን፣ ዳሰነች ወረዳ በሚያዝያ ወር 2012 በወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት በኩል ምዝገባ የተደረገላቸው 62 ሺህ 790 ተፈናቃዮች ሲሆኑ በኅዳር ወር 2016 ዳግም በተደረገው ምዝገባ የተፈናቃዮች ቁጥር 79 ሺህ 828 ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በአፋጣኝ ማቅረብን ጨምሮ፣ ተፈናቃዮች እና ነዋሪዎች ወደ ዘላቂ ሰላም የሚመለሱበት ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል