የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ወደሚገኝ “መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ” የተወሰዱ እስረኞች ብዛት 53 መሆናቸውን አስታውቆ ነበር
የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማስቆም፣ በጥሰቶች ተሳታፊ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እና ለተጎጂዎች ተገቢ የሆነውን የካሳ ሥርዓት ለመዘርጋት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ በሚገኝ ጊዜያዊ ማቆያ ማዕከል ውስጥ ተላላፊ በሽታ ተከስቶ የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ